ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች መታሰራቸው
የኢትዮጵያ ፖሊስ የሐገሪቱን ሠላምና ፀጥታ ለማደፍረስና ሕገ-መንግሥታዊዉን ሥርዓት ለማፍረስ አሲረዋል ያላቸዉን አራት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አንድ ጋዜተኛን አሰሠረ።
ፖሊስ እንደሚለዉ ተጠርጣሪዎቹ የታሠሩት በአሸባሪነት ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሐገሪቱን ለማወክ መዶለታቸዉን የሚጠቁም መረጃ ሥለደረሰዉ ነዉ።ሰወስት አባባላቱ የታሠሩበት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ግን የፖሊስን መግለጫ አጣጥሎ ነቅፎታል።ፓርቲዉ እንዳስታወቀዉ አባላቱን ለማስፈታትና የሕዝብን ነፃናት እና መብት ለማስከበር የሚያደርገዉን ትግል ይቀጥላል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ የኢትዮጵያ መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና ጋዜጠኞችን በሸባሪነት ጥርጣሬ ማሰሩን አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ተቃወመዉ።በድርጅቱ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይ አጥኚ ክሌር በስተን ዛሬ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰዎችን በአሸባሪነት ስም የሚያስረዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፥ የመብት ተቆርቋሪ ተቋማትንና ጋዜጠኞች የሚያስመቱትን ቅሬታና ተቃዉሞ ለማፈን ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት የእስረኞቹን ሕጋዊ መብት እንዲያከብርም በስተን ጠይቀዋል።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ክሌር ቤስተንን አነጋግሮ የላከልን ዘገባ አለ።
* ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች መታሰራቸው – ያዳምጡ
* የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ የምንስቲ ተቃዉሞ – ያዳምጡ