አንድነት – “አንዱዓለም እና እስክንድር ነጋ ታሰሩ ፤ አምባገነንነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያበቃ መታገል ያስፈልጋል”

መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም

ዛሬ ከቀኑ አሰር ሰዓት (10፡00) አከባቢ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አንደዓለም አራጌ በአገዛዙ የዯህንነት ሰዎች ታስሮዋል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም ተይዞዋል፡፡ አንደዓለምና እስክንድር ከሌሎች ሁለት የአንድት ፓርቲ አባለት ጋር ከቀኑ 8፡30 ገዯማ ጀምሮ አንድነት ፓርቲ አከባቢ በሚገኝ ካፍቴሪያ አከባቢ እሰከ 9፡30 ገዯማ አብሮ ሲጫዎቱ ነበር፡፡

አንድነት ፓርቲ የራሱን ስትራቴጂ ነድፎ፣ በጠራ የትግል አቅጣጫና በከፍተኛ የትግል ሞራል በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ ትግሉም የራሱ ዋጋ እንዯሚያስከፍል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ትግሉ አምባገነኖች ሊቀለበሱት ወዯማይችሉበት ዯረጃ በተቻለ ፍጥነት ማድረስ ያስፈልጋል፡፡

ለዚህም አንድነት በጀመረው የሠላማዊ ትግል መንገድ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ለሚዯረገው ትግል፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህብረት በመነሳት በሀገራችን አምባገነንነት ለአንዴና ለመጨረሺያ ጊዜ እንዱያበቃ መታገል ያስፈልጋል፡፡