አቡጊዳ – ጋዜጠኛ እስክንድር ታሰረ

መስክረም 3 2004 ዓ.ም

እውቁ ጋዜጠኛ እስክድንር ነጋ፣ ዜጎችን የማሸበርን ተግባር በተያያዙት የወያኔ ታጥቂዎች፣ መታሰራቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

ከጥቂት ሰዓታት በፊት፣ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ አቶ አንዱዋለም አርጌ መታሰራቸዉን መዘገባችን ይታወቃል።

ትግሉ ወደ ሰላማዊ ትግል መሸጋገር እንዳለበት የሚገልጽ ጽሁፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ያቀረቡት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ፣ ገዢዉን ፓርቲ በተለያዩ ጊዜያት ለእርቅና ለሰላም እንዲዘጋጅ ጥሪ ያቀረቡ እና የአገሪቷን ሕገ መንግስት በመጥቀስ የተለያዩ የፖለቲካ ትንታኔዎችን በማቅረብ የታወቁ ናቸዉ።

አቶ እስክንድር ን ነጋ፣ በቃሊቲ እሥር ቤት የተወለደች የአንዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆኑ ፣ የአንጋፋዋ ሌላ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ባለቤት ናቸዉ።

የአቶ እስክድንር እና የአቶ አንዱዋለም መታሰር ገዢዉ ፓርቲ አገር ቤት በሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል መደንገጡን የሚያመለክት እንደሆነ አስተያየት የሰጡን አንድ የፖለቲካ ተንታኝ “እስክንድርም ሆነ አንዱዋለም፣ ከዚህ በፊት በቃሊቲ የታሰሩ፣ ሊገደሉና ሊታሰሩ እንደሚችሉ ከወዲሁ ያወቁ፣ እንደዚያም ሆኖ ግን ለአገራቸዉ እራሳቸዉን መስዋእትነት አድርገዉ ያቀረቡ ጀግናና ቆራጥ ወጣት ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ” ሲሉ ለነዚህ ታሳሪ ወገኖች ያላቸዉን ከበሬታ ይገልጻሉ።

አዲሱ አመት ከመግባቱ በፊት ገዢዉ ፓርቲ ፣ ዝነኛና ተወዳጅ የሆነዉን ኢትዮጵያዊ አርቲስት ደበበ እሸቱንም ማሰሩን መዘገባችን ይታወቃል።