በሳውዲ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በራሳችን ላይ እርምጃ መውሰድ እንጀምራለን ሲሉ አስጠነቀቁ

በአንድ እስረቤት ውስጥ የሚገኙ 400 ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዳወጡት በተነገረለት መግለጫ ላይ እስረኞቹ በሁለት ቀናት ውስጥ የሳውዲ ወይንም የኢትዮጵያ መንግስት ለጥያቄዎቻቸው መልስ ካልሰጣቸው በራሳቸው ህይወት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

እነኝህ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች፣ ጓደኞቻቸው በየጊዜው በበሽታ ማለቃቸውንና በተፈጸመባቸውም ኢሰባዊ አያያዝ ምክንያት እነሱንም በራሳቸው ላይ እርምጃ እንዲወስዱ እንደሚገፋፋቸው ተናግረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደረሰን መረጃ እንደጠቆመው ወደ 6ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ እስርቤቶች እንደሚገኙ ፣ ከእነዚህም ውስጥ 2 ሺ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በቁጥጥሩ ስር የሚገኙ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሌት ከቀን በልማት አደግን፤ ከድህነት ተላቀቅን በማለት ይለፍልፍ እንጂ በኢትዮጵያ ያለው አስከፊ ችግር ዜጎችን ለስደት መዳረጉን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል።