ሠሎሞን ተካልኝ – ኢትዮጵያዊው ኦባማ ገርል

አሪስ ታታሊስ

ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሁላችንም የቅርብ ትዝታ ነው። የፓርቲ ዕጩነቱን ከማሸነፍ አንስቶ እስከ መጨረሻው የኖቬምበር 4 ምርጫ ድረስ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ የነበረ ምርጫ ነበር። ታዲያ በዚህ ምርጫ ወቅት ነበር አንዲት ኮረዳ ጎልታ የወጣችው። ስሟ አምበር ሊ ይባላል፤ አሁን ሁሉም በቅጽል ስሟ ”ኦባማ ገርል” እያለ ይጠራታል።