ኢትዮጵያዉያን ገበሬዎች “አርሶ አደርነት ዋጋ ቢስ ሆኗል” ሲሉ አማረሩ
በተለየያዩ ክፍላተ ሃገራት በሚኖሩ ገበሬዎች ዘንድ አሰሳን ያደረገው የግንቦት 7 ድምጽ ጋዜጠኛ ለዝግጅት ክፍላችን ባደረሰው መረጃ እንደዘገበው፥ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ያናገራቸው ገበሬዎች ስለ ኑሯቸው ያማርራሉ።
በተለይም በአማራ ክልል ያሉ ገበሬዎች እህል የሚሸጡበት ዋጋ ከወጪያቸው ጋር ባለመመጣጠኑ አርሶ መብላት ለነሱ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ዋጋ ቢስ ሆኗል።
ከዚህ የተነሳ የማዳበሪያ እዳ እና ግብር መክፈል አለመቻላቸው ደግሞ መሬታቸው ከዛሬ ነገ ይነጠቃል በሚል ስጋት ስር እንዲኖሩ አድርጓቸዋል። ይህንን የገበሬዎቹን ፍርሃት የሚረዱት የወያኔ ካድሬዎችም፣ ጉዳዩን እንደማስፈራሪያ እየተጠቀሙ ገበሬዎቹ ያለነሱ ፈቃድ መኖር እንደማይችሉ እንደሚያስታውሷቸው ለማወቅ ተችሏል።