ፍኖት ጋዜጣ – ጋዜጠኛ ዉብሸትንና ርዮት አለሙን በተመለከተ የቀረበ ሪፖርት
የታሰሩት ጋዜጠኞች የምርመራ ጊዜ መራዘሙ የከረረ ተቃውሞ ገጠመው።
የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ድብደባ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተወሰነ።
“በሽብርተኝነት” ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮና ርዕዮት ዓለሙን ታስረው በሚገኙበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ጠይቀናቸው ነበር፡፡ ተጠርጥረው በታሰሩበት ። “የሽብርተኛ ድርጊት” ስለተባለዉ የሚያውቁት ነገር መኖር አለመኖሩን ጠይቀናቸው ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ውብእሸት ሲመልስ “የቀረበልኝ ጥያቄ በተደጋጋሚ የብተና ፖለቲካ አያልክ ትጽፋለህ፡፡ በታኙ ማን ነው፡፡ ብተና የሚፈልገው ማነው? መንግሥት ኮሚኒኬሽን ሰርገህ ለመግባት የፈለክበት ምክንያት ምንድነው? ውጭ አገር ከሚገኝ አንድ ሚዲያ ጋር ለምን ትገኛለህ? የሚሉ ናቸው፡፡ “ሽብርተኝነት” የሚለውና “ንብረት ሊያወድም” ነበር፡፡” የሚለውን የሰማሁት በሚዲያ” ነው ሲል መልሷል፡፡
ጋዜጠኛ ውብእሸት /እየሳቀ/ “ከቤቴ ለምርመራ የተወሰዱት መጽሐፍት እነ ተክለጻዲቅ መኩሪያ የጻፉትን የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡ በዚህ ላይ የእኔ ጥፋቱ አልገባኝም፡፡ እየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል የሚያሳይ የስቅለት ፊልምና እና ልጄ ሁለተኛ ዓመት ልደቱን አክብሮ ድክ ድክ ሲል የተቀረጸ ፊልም ለምርመራ ብለው ከቤቴ ወስደዋል፡፡ ምናልባት እየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል እጅህ አለበት፡፡ ልጅህም በሽብርተኝነት ይጠረጠራል አንዳይሉኝ እሰጋለሁ፡፡” ሲል በለሆሣስ ገልጾታል፡፡
በመጨረሻም ጋዜጠኛ ውብሸት “የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉደዮች ጽ/ቤት ሠራተኛ ይቀጠላል በመባሉ የትምህርት ማስረጃና የሥራ ልምዴን ከማመልከቻ ጋር አስገብቼ ነበር፡፡ ሳይሳካ በመቅረቱ ቀርቷል፡፡ እኔ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሥራ የመወዳደርና የመቀጠር መብት አለኝ ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ዛሬ ወንጀል ሆኖ ለምን መስረግ ፈለክ ተብሎ በምርመራ ወቅት መጠቀሱ አሳዝኖኛል፡፡ በእስር ላይ እያለሁ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡ የግራ ጆሮዬ ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል፡፡ በትክክልም አይሰማም” ሲል በሐዘኔታ ገልጾታል፡፡
የፍኖት አምስተኛ እትምን በሙሉ ለማንበብ በወደ አንድነት ፓርቲ ድህረ ገጽ ይሂዱ