የአለም የገንዘብ ተቁአም ኢትዮጵያን ያልታደለች ሃገር ሲል ገለጸ፣ በሃገሪቱ ሁኔታዎች ከመሻሻል ይልቅ እየትባባሱ ነው አለ

በምህጻረ ቃሉ አይ ኤም ኤፍ በመባል የሚታወቀው የአለም የገንዘብ ተቋም የወያኔው ዘረኛ አገዛዝ ፖሊሲ የፈጠረው የዋጋ ግሽበት ከቁጥጥሩ ውጭ እየሆነ በመምጣቱ ኢትዮጵያን ያልታደለች ሃገር ሲል የገለጸ ሲሆን፣ በሃገሪቱ ሁኔታዎች ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሱ መምጣታቸውን ባወጣው ሪፖርት ላይ ገልጹአል።

ለወያኔ ቅርበት እንዳልዉ የሚታወቅለት የሪፖርተር ጋዜጣ በ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ የዓለም ባንክ የዉስጥ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ እ.ኤ.አ ከኅዳር 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ሚዛኑን እየሳተና እየተበላሸ መምጣቱን በማሳሰብ አይኤምኤፍ የወያኔን አገዛዝ ክፉጛ የሚያወግዝ ሪፖርት ማዝጋጀቱን አጋለጠ፡፡ ሪፖርቱ ጠንካራ ቃላትንም በመጠቀም ዘረጛዉን የወያኔን አገዛዝ በተጠያቂነት ክፉኛ የተቸ መሆኑ፣ ብስጭት የፈጠረበት የመለስ አገዛዝ ሪፖርቱ ለአባል አገሮችና ለሕዝብ በኢንተርኔት እንዳይሰራጭ ያገደ መሆኑንም ገልጹአል፡፡

ይሕ ለህዝብ ይፋ እንዳይደረግ በወያኔ ታገደዉ የአይኤምኤፍ ሪፖረት ባሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለና ለዚህም በዋናነት ምክንያት ነዉ ያለዉ ካለፉት ሁለት ዓመት ወዲህ እየጨመረ የመጣወንና ባሁኑ ጊዜ 40% የደርስዉን የዋጋ ግሽበትን ነዉ።- ለዋጋ ግሽበቱም መባባስና አሁን ካለበት ደረጅ ያደረሰዉ፣ የባንክ የወለድ ምጣኔ ከዋጋ ግሽበት በታች መሆኑ (Highly Negative Real Interest Rate) ፣ ከዚህ በተጨማሪ የወያኔ ልማት ድርጅት ተብዬዎች በርካሽ ወለድ ከባንኮች የሚበደሩት ብዛት ያለው ገንዘብ መሆኑን በሪፖርቱ ውስጥ አካቷል፡፡ የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ከኬንያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከታንዛኒያና ከሰሀራ በታች ካሉ አገሮች የዋጋ ግሽበት ጋር ሲነፃፀር በአራት እጅ እንደሚበልጥ አይኤምኤፍ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

የዋጋ ግሽበቱን አስመልክቶ የወያኔዉ ባለሥልጣናት የተምታታና ወጥ ያልሆነ ምክንያት በማቅረብ ላይ እንዳሉም ታዉቁአል። ለዚህም የወያኔዉ ባለስልጣናት ልል የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ (Loose Monetary Policy) እንደሚከተል ሲያምን፣ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱ ዋነኛ ምክንያት ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የገባ የዋጋ ግሽበት ነው ብሎ እንደሚያምንና አይኤምኤፍም ይኼንን የክርክር ነጥብ ውድቅ እንዳዳረገው በሪፖርቱ ውስጥ እንደተገለጠ ም ጠቁሙአል፡፡ይልቁንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚያሳትመው ገንዘብ (Base Money) በዓመታዊ ንፅፅር 42 በመቶ መጨመሩን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የሰጠው ብድር የ45 በመቶ ጭማሪ በማሳየቱ ለዋጋ ግሽበቱ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን አይኤምኤፍ በሪፖርቱ ውስጥ አሳይቱአል።

አይ ኤም ኤፍ ለማክሮ ኢኮኖሚዉ አሉታዊ የሆኑ አሳሳቢ ጉዳዮች በማለት የተቸዉ የወያኔ አገዛዝ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን በተመለከተ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለጥናት የሚያወጣቸዉ የቁጥጥር መመርያዎች የዘርፉን እንቅስቃሴ እየገቱና እምነቱን እየጐዱ (Damaging Private Sector Confidence) መሆኑንም ነዉ። አገዛዙ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ በተለይም በፋይናንሱ ዘርፍ በተሰማሩት ላይ የሚያደርሰዉ ን ጫና ለማሳየት ዋቢ ያድርገዉ እ.ኤ.አ ከሚያዚያ 2010 ወዲህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ንግድ ባንኮች ካበደሩት ብድር ውስጥ 27 በመቶ የሚሆነውን የብሔራዊ ባንክን ቢል (ቦንድ) እንዲገዙ በማስገደዱ፣ ይኼ መመርያ ከወጣ ወዲህ የግል ባንኮች በአምስት በመቶ ወለድ ከአስቀማጮች ካሰበሰቡት ገንዘብ ዉሳጥ 27 በመቶ የሚሆነውን በሦስት በመቶ ወለድ ለብሄራዊ ባነኩ እንዲያበድሩና ብሔራዊ ባንክም ከግል ባንኮቹ ያገኘውን ገንዘብ በወያኔ ቁጥጥር ስር ላሉት ለኢትዮጵያ ልማት ባንክና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመስጠት፣ የማበደር አቅማቸውን እንዲያጠናክሩና እንዲያተርፉ ማድረጉ ፍፁም ኢ/ፍትሐዊ ና የፋይናንስ ተቋማትን ዕድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን በሪፖርቱ ውስጥ ካካተታቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነና ነው፡፡

የወያኔዉ አገዛዝ ኢኮኖሚው ዘንድሮ በ11 በመቶ ማደጉንና በቀጣይ ዓመታትም ይኼንኑ ዕድገት እንደሚያስቀጥል ቢጠቅስም፣ አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ወደ6.5 በመቶ እንደሚወርድ ትንበያውን አስፍሯል፡፡

አይኤምኤፍ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚከተለው ልቅ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲና ብር እያተመ ከማሰራጨት ተግባሩ እንዲታቀብ፣ የወለድ ምጣኔን እንዲያስተካክል፣ የኢኮኖሚ መዋቅር ማሻሻያዎችና የንግድና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የወያኔን ገዢዎች መምከሩን፣ ቀደም ብለን መዘገባችን አይዘነጋም።

አይ ኤም ኤፍም በማጠቃለል ሁኔታዎች ከመሻሻል ይልቅ ተባብሰው የተገኙ መሆናቸውን በማስታወስ አለመታደል (Unfortunate) ነዉ ሲል ማስፈሩን ለማወቅ ተችሎአል፡፡

ሪፖርቱ ጠንካራ ቃላትን በመጠቀም የወያኔን ባለስልጣኖች ክፉኛ የተቸ በመሆኑ፣ ለአባል አገሮችና ለሕዝብ በኢንተርኔት እንዳይሰራጭ አገዛዙ ያገደ መሆኑን የገለጠዉ ሪፖርተር ይሁን እንጂ የአይኤምኤፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሪፖርቱ ላይ አቋም ሳይዝ እንዳልቀረም የዓለም ባንክ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያይዘም እንደአውሮፓዊያን አቆጣጠር ሜይ 31 ቀን 2011 አይ ኤም ኤፍ በተመሳሳይ ዘገባው አገዛዙ ያወጣው የአምስት አመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሊሳካ የማይችልና ላም አለኝ በሰማይ በሰማይ አይነት እንደሆነ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል::