ዘረኛው አገዛዝ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ባለስልጣናትን ማስወገድ ቀጥሉአል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አፈ-ጉባኤ ና ሎሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተረኛዎች ሆነዋል

ለሚፈልገው አላማ መሳካት አንድ ወቅት ስልጣን ላይ ያስቀመጣቸውን ሆድ አደሮች እንደሸንኮራ አገዳ መጥጦ በመጣል የሚታወቀው የዘረኛ አገዛዝ ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አፈ ጉባዔ ሆኖ በመሥራት ላይ የሚገኘውን ሀብታሙ ኢካ ፈለቀ፣ በሙስና ወንጀል ወደ እስር ቤት ማስገባቱን ሪፖርተር በመባል የሚታወቀውና ለአገዛዙ ቅርበት ያለው ጋዜጣ ዘገበ፡፡

እንደ ሪፖርተር ዘገባ ሀብታሙ ኢካ በቁጥጥር ሥር የዋለው፤ የክልሉ ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ያለመከሰስ መብቱ ከተነሳ በኋላ ሲሆን ከአፈ ጉባዔው ጋር የተጠረጠሩ በርካታ ባለሥልጣናትና ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር እየዋሉ እንደሆነ ታውቁአል፡፡

በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የአካባቢ ተወላጆችን በስልጣን ወምበር ላይ እንዲቀመጡና የሚፈልገውን እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚታወቀው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናቱ፣ ከቁጥጥር እንዳይወጡ አንገታቸውን ማስደፊያ የሚሆን እንደሙስና ባሉ ወንጀሎች እንዲዘፈቁ እንደሚያደርግና፣ ባለስልጣናቱ አገልግሎታቸውን ሲያጠናቅቁ በወንጀል ወደ ዘብጥያ ሲያወርድ እንደቆየ በተደጋጋሚ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል::