ባምቢስ ሱፐር ማርኬት ታሸገ

– ጊዜያቸው ያለፈባቸው እሽግ ምግቦችና መጠጦች ተገኝተዋል

ባምቢስ ሱፐር ማርኬት ከውጭ የሚገቡና ጊዜያቸው ያለፈባቸው እሽግ ምግቦችንና መጠጦችን ለተጠቃሚዎች ይሸጣል በሚል ተጠርጥሮ ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ታሸገ፡፡