አድባር፡ ሶስተኛውን ክርክር በቶሮንቶ አዘጋጅቷል
ዲሜጥሮስ ብርቁና ተክሌ አበበ መርጋ ይከራከራሉ
Ethiopia Zare (አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2003 ዓ.ም August 26 2011) :- ባለፈው ግንቦት የተቋቋመውና መቀመጫው በቶሮንቶ የሆነው “አድባር የክርክር ማህበር” ሶስተኛውን የክርክር ዝግጅት በያዝነው ሳምንት፡ አርብ፡ ኦገስት 26 ከሰዓት በኋላ፡ ከ5 ሰዓት ጀምሮ፡ በሂሩት የሀበሻ ሬስቶራንት እንደሚያደርግ በላከው አጭር መግለጫ አስታወቀ።