ለትምህርት ጥራት መጓደል የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች ተተቹ

‹‹የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የግድ የትምህርት ባለሙያ መሆን አያስፈልግም›› ረዳት ፕሮፌሰር ወንድወሰን ታምራት

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በቴክኒክ ትምህርት ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከግብርና ጋር ተያያዥነት ካላቸው የትምህርት መስኮችና ሥልጠናዎች ስፔሻላይዝ ያደረጉ በመሆናቸው፣ ለትምህርት ጥራት ችግር የመጀመሪያዎቹ መንስዔዎች መሆናቸውን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡