የቀድሞ የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንት ተፈረደባቸው

– ሦስት ተከሳሾች በገደብ ተለቀቁ

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች፣ ጥፋተኛ በተባሉበት ወንጀል ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ከሁለት ወራት በሚደርስ ፅኑ እስራትና በገንዘብ በትናትናው ዕለት ተቀጡ፡፡