በብድር እጦት ቡና አምራቾች ጫት ልናመርት ነው አሉ

– ማኅበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ ጻፈ

በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን የሚገኙ የቡና ገበሬዎች ባንኮች ብድር ባለማቅረባቸው ምክንያት፣ እርሻቸውን ወደ ጫት እየለወጡ መሆኑን የሲዳማ ቡና አቅራቢዎች ማኅበር አስታወቀ፡፡