ኧልሸባብ የምሥራቅ አፍሪቃ ስጋት

ኧልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ፅንፈኛ ቡድን ቅዳሜ፣ መስከረም 11 ቀን 2005 ዓም ኬንያ መዲና ናይሮቢ በሚገኝ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ውስጥ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 72 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። በገበያ አዳራሹ የነበረው የእገታ ርምጃ ከአራት ቀናት ቆይታ በኋላ መጠናቀን ታውቋል። ለመሆኑየኧልሸባብ ማንነት እና አነሳስ ምን ይመስላል?