ርዮት አለሙ በሕመም ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ!
(ፍኖት) – «በሽብርተኝነት ተጠርጥራ.» በፌደራል ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛና መምህርት ርዮት ዓለሙ በህመም ላይ እንደምትገኝ ወላጅ አባቷ አቶ ዓለሙ ጐቢቦ ለፍኖት ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገለጹ፡፡ አቶ ዓለሙ እንዳሉት ርዮት በህመም ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ መድኃኒት ገዝተዉ እንዳስገቡላትም ገልጸዋል።። ሰውነቷ በህመም መጐሳቀሉንና ሐሳቧም በእጅጉ ከመበታተኑም በላይ ከዚህ በፊት ያልነበረባት የመዘንጋት ባህርዬ የተፈጠረባት መሆኑን የገለጹት አባቷ «ጤንነቷ በጣም አሳስቦናል..» በማለት ጭንቀታቸዉን ገልፀዋል፡፡
ርዮተ ዓለሙ በቋንቋ መምህርነትና በትያትርና ሥነ ጥበብ ሁለት የመጀመሪያ ዲግሪዎች ያላት ሲሆን በ2004 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኢትዮጵያ ሁለተኛ ዲግሪዋን /ማስተርስ/ ለመማር ተመዝግባ እንደነበር ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል፡፡
ርዮት ዓለሙ እናቷንና እህቷን የምታስተዳድር ሲሆን በመታሰሯ ምክንያት ደሞዟ መቋረጡን ከቤተሰቦቿ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የፎነት ለነጻነት እትም ሁለት በሙሉ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ