በባንክ ዕዳ ሲፈለግ -የሸፈተው “ታጋይ”

ሲሳይ አጌና

“አባባ ታምራት፣አርቲስቶቻችን እና የህዳሴው ግድብ”) በሚል ርዕስ ባለፈው ባቀርብኩት ጽሁፍ ላይ ያልተቋጨ እና በይደር የተውነው ነገር መኖሩ ዕውነት ነው፤በዚያ ጽሁፍ ላይ የሰዎቹ ስም ባለመጠቀሱ ቅር ያላቸው፣ልብ ወለድም የመሰላቸው አጋጥመውኛል፤በኤሌክትሮኒክስ የመልዕክት ሳጥኔ ውስጥ::እንከሳለን ያሉም ጽፈውልኛል ፤ክሱ ሄግ ይሁን ልደታ ባይታወቅም።እርቃን ዳንስ ቤት የተገኘው ሚንስትር ማነው? ኮተቤው ጠንቋይ ቤት የተገኘውስ ? የአባባ ታምራት ደንበኛ የነበሩትስ እነማን ናቸው.? ….ከባንክ ብድር ወስዶ በዕዳ ሲፈለግ ጫካ የገባውስ ማነው ?ዛሬስ የየትኛው ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ነው የሆነው? ኢህአዴግን ስትከዳ በኢሕአዴግ ማጋጣነቷ የተጋለጠባት ማነች? የሚሉት ጥያቄዎች በርክተቢመጡም ለሁሉም ምላሽ መስጠት ባለመቻሌ አዝናለሁ፤የቢዮንሴን ጫማ ያደረገላት ሰው ማንነት የብዙዎቹን ትኩረት መሳቡ ግን ያልጠበኩት ነበር።