ፍኖት – የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ጊዚያዊ ም/ቤት ተቋቋመ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ / አንድነት/ የአዲስ አበባ ከተማ ጊዚያዊ ም/ቤት መቋቋሙን የፓርቲው ም /ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ አስራት ጣሴ ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ አቶ አስራት እንዳሉት ከአዲስ አበባ 23ቱ የምርጫ ወረዳዎች ሁለት ሁለት ተወካዮች ተወክለው በ46 የም/ቤት አባላት ጊዛዊ ም/ቤት ተቋቁሟል ብለዋል፡፡ ከም/ቤቱ አባላት መካከል ም/ቤቱን የሚመሩ 10 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መመረጣቸውን ለማወቅ ተችሎአል፡፡ በተደረገውም ምርጫ ዶ/ር ንጋት አስፋው ሰብሳቢ፣ አቶ ደምሴ መንግስቱ ም/ሰብሳቢ፣ አቶ በቀለ ወ/ሚካኤል ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ስለ ም/ቤቱ ቀጣይ ሥራ የጠየቅናቸው የም/ ቤቱ ስብሳቢ ዶ/ር ንጋት እንዳሉት የም/ቤቱ ቀዳሚ ሥራ በአዲስ አበባ 23 የምርጫ ወረዳዎች ቋሚ ም/ቤቱን ለማቋቋም መታሰቡን ገልፀዋል፡፡

የፍኖት የመጀምሪያዉ እትም ጋዜጣን በሙሉ በፒ.ዲ.ዔፍ ለማንበበ ከዚህ ይጫኑ