የኦታዋው ግልጽ ህዝባዊ ስብሰባ፡ በስውር ተጠናቀቀ
“የብሄር ድርጅቶችን፡ አቅርቦ መያዝ እንጂ፡ ሙሉ በሙሉ ማግለሉ አግባብ አይደለም” እኔ
“የብሄር ድርጅቶችን እንደውም መድረክ በመስጠት ማጠናከር ሳይሆን ማጥፋት ነው” አንድ ተሳታፊ
“የኢትዮጵያን አንድነት የማይቀበሉ የብሄር ድርጅቶችን እንደውም ወደፊት እንደወያኔ የምንዋጋቸው ናቸው” ዶ/ር ኤርሚያስ ዓለሙ
ልዩ ዘገባ – ልጅ ተክሌ (ኦታዋ-ካናዳ)
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2003 ዓ.ም. July 14, 2011):– እሁድ ጁላይ 24፡ 2011 ዓ.ም.፡ መቀመጫው በኦታዋ የሆነው፡ “የኢትዮጵያ ካናዳዊያን መድረክ ለዴሞክራሲ” (በእንግሊዘኛው “Ethio-Canadians Forum for Democracy”፡ ከፖለቲካ እስረኞች አንድነት ማህበር፡ ከኢህአፓና፡ ከዓለም-አቀፋዊው የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር ምስረታ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በመተባበር፡ በኦታዋ ያዘጋጀው ስብሰባ የተለያዩ፡ ሀሳቦች ተንሸራሽረውበት ተጠናቀቀ። ዝግጅቱ ግን እንዳይቀረጽ መከልከሉ ጥቂቶችን አስቆጥቷል።