የህይወቴ ታሪክ – ከፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ተክለማሪያም

ቅኝት በመስፍን ማሞ (ክፍል ሁለት)  
 
አንባቢ ሆይ በእንደኛው ክፍል የፊታውራሪ ተክለሃዋሪያት ኦቶባዮግራፊ ቅንታችን ከሳያደብር የተነሳው ታዳጊ በእንደምን ያለ ሁኔታ አዲስ አበባን ረግጦ፤ ሀረር አድጎ፤ አደዋ ዘምቶ፤ ሰነባብቶም ውቅያኖስ አቋርጦ፤ አድማስ ዘልቆ፤ ሩሲያ እንደኖረና በትምህርት ዳብሮ፤ በአስተሳሰቡ በልጽጎ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ ተመልክተናል። ሁለተኛውንና ማሳረጊያውን ክፍል ሁለት ደግሞ እነሆኝ ብለናልና አብረን እናዝግም…