ክርክር፥ ባህላችን በፖለቲካችን ላይ ያለው አንድምታ

«ባህላችን የሁለንተናዊ ማንነታችን መሠረት ነውና እሱን ይዘን እንከኖቹን ነቅሰን ማሻሻልና ማጎትበት እንችላለን፤» የሚለውን መከራከሪያ የያዘ ተከራካሪ በአንድ ወገን «የለም ባህላችን፤ ይልቁንም ደግሞ የፖለቲካ ባህላችን መሠረታዊ ለውጥ ይሻል፤ ዛሬ ላሉን ችግሮችም የአንዳንዱ መነሻ ነውና ከሥር መሠረቱ መቀየር አለበት፤» የሚለውን የያዘው ደግሞ በሌላው ተሰልፈዋል።

የክርክሩ ተሳታፊዎች የቶሮንቶ ካናዳ ነዋሪዎቹ ዳንኤል ጥላሁንና ኪሩቤል ፍሬው  ናቸው። በቅርቡ ባቋቋሙት «አድባር የክርክር መድረክ፤» በተሰኘው ማኅበራቸው ከተሟገቱባቸው ርዕሶች አንዱ የሆነው ይኸ የመከራከሪያ ነጥብ ነው የምሽቱም እሰጥ አገባ መንደርደሪያ።

የክርክሩን የመጀመሪያውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤