የምስራቅ ኢትዮጵያ አስከፊ ረሃብ አሳሳቢ ሆኗል

ሊያነቡት የሚገባ ልዩ ዘገባ – ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. July 14, 2011):- ህጻናት ረሃብ ሳል እአሰሙ ነው። እናቶች የልጆቻቸውን አሰቃቂ ሞት በአይናቸው ለማየት ተገደዋል። እርፍ ጨብጠው መሬቱን እገመሰ ዘርቶ፣ አችዶና ሰብስቦ ለሌላው ይተርፍ የነበረው ገበሬ ተስፋ የቆረጡ አይኖቹ እንባቸው ደርቋል። ለሰው ልጆች ተስፋ የነበሩት ዕጸዋት ጠውልገዋል።ከብቶች በሜዳው ላይ ወድቀዋል። የተስፋ ጭላንጭል ተዳፍኖ የሞት ደመና በሚሊየኖች የሚቆሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አንዣቧ።