የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት ቅዳሴ ቤት ተከበረ

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 8/2010፤ ጳጉሜን 3/2002 ዓ.ም):- በሀገረ ጀርመን የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት ቅዳሴ ቤት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ በመት ደማቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ፡፡
ነሐሴ 23 እና 24 ቀን 2002 ዓ.ም. የተከበረው በዓል ልዩ ልዩ መንፈሳውያት ዝግጅቶች የቀረቡበት ነበር፡፡ ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2002ዓ.ም. ከመላ ጀርመን የተሰባሰቡ ካህናትና ምእመናን የተሳተፉበት ዐውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በዐውደ ጥናቱ „የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምሥረታና ታሪክ በሀገረ ጀርመን“ በሚል ርእስ በመልአከ ሰላም ዶ.ር መርዐዊ ተበጀ፤ እና “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታ” በሚል ርእስ በዲ.ን ዶ.ር መርሻ አለኸኝ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምእመናኑ ተወያይተውባቸዋል፡፡ ከዐውደ ጥናቱ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጀርመን ከምሥረታዋ ጀምሮ እስከ አሁን ያደረገችውን የአገልግሎት ጉዞ የሚያስቃኝ ዐውደ ርእይ ተከፍቶ በምእመናኑ ተጎብኝቷል፡፡ የሕጻናት ዐውደ ትእይንትና ልዩ ልዩ መንፈሳውያት ቁሳቁሶች ለሽያጭ የቀረቡበት ባዛርም የዕለቱ መርሐ ግብር አካላት ነበ፡፡
በመጨረሻም የሰርክ ጸሎትና ስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ተከናውኖ ካህናቱ ወደ ማረፊያቸው ከተሸሁዋላ በዓሉን ለማክበር ከመላ ጀርመን የተሰባሰቡ ምእመናን ሲማማና በመዝሙር እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ አድረዋል፡፡ እሑድ ነሐሴ 24 ቀን 2002ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መሪነት ለዕለቱ የሚያስፈልጉት ልዩ ልዩ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽመው ሥርዓተ ቅዳሴው ከተከናወነ በላ የቃል ኪዳኑ ታቦት በታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ከብሯል፡፡ በሥርዓተ ንግሡም ልዩ ልዩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክቶች ተላልፈዋል፡፡
በዓሉን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በጽሑፍ ያስተላለፉት መልእክት በቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ የበርሊን ቅ/አማኑኤልና የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ በንባብ ተሰምቷል፡፡ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በሐምቡርግና አካባቢ የሚኖ ምእመናን ከሚያገለግሏቸው ካህናት ጋር በመተባበር ለዚህ ደረጃ በመድረሳቸው “እንኳን ደስ አላችሁ” ካሉ በላ ለወደፊትም በፍቅርና በአንድነት በመኾን ቤተ ክርስቲያናቸውን የበለጠ እንዲያጠናክ አደራ ብለዋል፡፡ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት መልአከ ሰላም ዶ.ር መርዐዊ ተበጀም “በሐምቡርግ ለሚኖ ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ከተጀመረ ሃያ ሁለት ዓመታት እንደ ተቆጠ” በማውሳት ጥረቱ ሁሉ ሰምሮ የአካባቢው ምእመናን ለዚህ በመድረሳቸው “እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ምእመናኑ ቤተ ክርስቲያናቸውን እዚህ ካደረሱ ዘንድ አሁንም የበለጠ በመጠናከር በመካከላቸው ተቀምጦ የሚያገለግላቸው ካህን ለማስመጣት እንዲተጉ አሳስበዋል፡፡ 
በተጨማሪም የሐምቡርግ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ሐላፊ የኾኑት ፓስተር ወ/ሮ ዜቨሪን ካይዘር ባስተላለፉት መልእክት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐምቡርግ መጠናከር ለእኛ ውበት ይጨምርልናል፡፡ ቤተ ክስርቲያናችሁ ውበት የተመላች ናትና አሁንም በርቱልን” ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ባስተላለፉት ቃለ ምእዳንና ትምህርት የበዓሉ ፍጻሜ ኾኗል፡፡ የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላትና የአጥቢያው ምእመናን በዓሉ በደመቀ ሁኔታ በመከበ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡