መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከትግራይ እስደ ደቡብ ክልል የውሃ ጀሪካኖችን በምንጮችና በውሃ መስጪያ ባንቧዎች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች የውሃ እጥረት ማጋጠሙን የየክልሉ ሪፖርተሮች ከሚልኩት እለታዊ መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚስጢር ሲያደርጉት የቆዩት ድርድር ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የሶስቱ አገር መሪዎች በተገኙበት በካርቱም እንደሚፈረም መረጃዎች አመልክተዋል። የፊርማ ስነስርአቱ የፊታችን ሰኞ በካርቱም የሚካሄድ ሲሆን፣ ዝርዝር ይዘቱ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ተደርጓል። የአባይ ግድብ  ከህዝብ በውዴታና በግዴታ በሚዋጣ ገንዘብ እየተገነባ መሆኑ እየታወቀ፣ ስምምነቱን ገንዘቡን ለሚያዋጣው ህዝብ ይፋ ለማድረግ ለምን እንዳልተፈለገ …

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ የ25ኛ አመት በአሉን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማክበር የነበረው ፍላጎት ከተደናቀፈ በሁዋላ፣ በደራ ወረዳ ጉንዶመስቀል ከተማ ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፣ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘግተው ሰራተኞች የገጠሩን ህዝብ እንዲቀሰቅሱ ተሰማርተዋል። መጋቢት 10 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጉንዶመስቀል ይገባሉ ተብሎ በመጠበቁ እጅግ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰራተኞች ወደ …

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎችን የሚያሰለጥነው አካዳሚ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ  በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመው  የአመራር አካዳሚ በመንግስት በጀት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ዙሮች 2ሺ 500 ያህል ከፍተኛ አመራሮችን፣ ከ30ሺ በላይ መካከለኛ አመራሮችን አሰልጥኗል፡፡ አካዳሚው ያለአንዳች ፈቃድ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ሲሰራ ከቆየ በሃላ በ2006 ዓ.ም …

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች በመወከል ድምጹ እንዲሰማለት ጠይቆ፣ መለስ የተነፈገው ድምጻችን ይሰማ አመራሮቹን ለማስፈታትና ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ግፊት ለማድረግ እስካሁን ሲከተለው ከነበረው የትግል ስልት አንድ ደረጃ ከፍ ያለ የትግል ስልት ይፋ እንደሚያድርግ አስታውቋል። ድምጻችን ይሰማ ” መብቴን ካላከበርክ እኔም..” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ህዝብ ሲመረው መብቴ ይከበርልኝ …

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሉ በአውስትራልያ ክዊንስላንድ ግዛት ነዋሪ በሆኑ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓም ተከብሯል። በበአሉ ላይ በግዛቱ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን የአድዋን ድል ታሪካዊነትን የዳሰሰ ሰፋ ያለ ዝግጅት ለታዳሚው ቀርቧል:: ዓድዋን አስመልክቶ በፕሮጀክተር በታገዘና በምስልና ድምጽ የተደገፉ ማስረጃዎች በቀረቡበት በዚህ ዝግጅት ላይ የዓጼ ምንሊክን …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ተቃውሞውን ያስነሱት መሬታቸው ለትምባሆ ተክል እርሻ ለአንድ ባለሀብት መሰጠቱን ተከትሎ ነው። በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚኖሩት ቁጥራቸው እስከ 5 ሺ የሚደርሱ የብሄረሰቡ አባላት፣ ቀደም ብሎ በአባያ ሃይቅ መካከል በሚገኘው ደሴት ይኖሩ ነበር። ደሴቱ በሃይቁ ሙሉ በሙሉ መሸፈኑን ተከትሎ የብሄረሰቡ አባላት ሃንቲ ወደ …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ክልሎችን የሚሸፍነው ሪፖርት፣ በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ዝርዝር ጥቃቶችን አቅርቧል።  በትግራይ ክልል በአጽቢወንበርታ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመድረክ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ወ/ገብርኤል ኃይሉ የዕጩነት መታወቂያ እንደያዙ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ የአስር ወራት የእስራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል፡፡  “በቆላ ተንቤን ወረዳ በወርቅ አምባ ምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ አረብ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ የሚደረገው ጉዞ  በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከአንድ ዓመት በፊት ከታገደ በሃላ ሕገወጥ ዝውውሩ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የሥራ ስምሪት ህጉ እስኪስተካከል ድረስ ለስድስት ወራት ብቻ ጉዞው እንዲታገድ መንግሥት ወስኖ የነበረ ቢሆንም፣  እገዳው  ሳይነሳ ከአንድ ዓመት ከአራት ወራት በላይ …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስምምነቱ መሠረት የዲፕሎማትና ሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ የሁለቱ ሀገራት ሰዎች ለ30 ቀናትና እንደአስፈላጊነቱ ሊራዘም የሚችል ቆይታ ያለቪዛ እንዲገቡ ይፈቅዳል፡፡ ይህን ቪዛን የሚያስቀረው ስምምነት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የሁለቱ ሀገራት ዜጎች ለስራ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እየጨመረ በመምጣቱ ነው ተብሎአል፡፡ በሁለቱ ሀገራት ስምምነት መሰረት ከምክትል ሚኒስትር በላይ የሆነ ማእረግ ያላቸው የማእከላዊ መንግስቱ ባለስልጣናትና …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሚቀጥለው ሳምንት ከመጋቢት 10 እስከ 13 ድረስ ባሉት ቀናት የአዲስአበባ አስተዳደር 20 በ80 ተብሎ የሚታወቀውን የኮንዶሚኒየም 35 ሺ ቤቶች ዕጣ በማውጣት ለእድለኞች ለማስተላለፍ ያቀደ ሲሆን በዚህ የዕጣ አወጣጥ ፕሮግራም ላይ 40 በ 60 የሚባለውና አብዛኛው ዲያስፖራ ተመዝግቦበታል የተባለው ዕጣ እንደማይወጣ ታውቆአል፡፡ የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሰሞኑን …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በብአዴን አመራሮች እና በግንባር ቀደም አርሶ አደሮቸ ላለፉት አምስት አመታት የወረቀት ፈብሪካ ለመገንባት በሚል ከተሸላሚ አርሶ አደሮች የተሰበሰበው በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገማ እንደማይታወቅ አርሶ አደሮች ተናግረዋል። ገንዘባቸው እንዲመለስልቸው ቢወተውቱም  ምላሽ ማጣታቸውን ተናግረዋል። በሰባተኛው የአርሶአደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው ዘጋቢያችን  …

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በአገሪቱ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲያመጣ፣ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚጠይቁ የብር  ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። ዜጎች በተለያዩ የብር ኖቶች ላይ ” ህዝባዊ እምቢተኝነት ይቀጥላል፣ ፍትህ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ከዘረኝነት የጸዳች አንዲት ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ ይሰማ፣ ፍትህ፣ ዘረኝነት ይብቃ፣ ጭቆና ይብቃ የሚሉና ሌሎችም መፍክሮች ተጽፎባቸው እየተሰራጩ ነው። 

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ  ትምህርት ቢሮ ባሰራጨው የጥሪ ወረቀት የተማሪዎች ወላጆች ስለክልሉ ሁኔታና ስለምርጫ እንዲሁም ልጆቻቸው ስላለባቸው ሃላፊነት ስልጠና እንዲወስዱ ያዛል። ስልጠናው እንዳበቃም ወላጆች ስርተፊኬት ይቀበላሉ። ስልጠናው ከትናንት ጀምሮ በመሰጠት ላይ መሆኑንም ወኪላችን ገልጿል።    

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባንና የኦሮምያን የጸጥታ ሁኔታ ለማስተሳሰር፣ የኦሮምያን ልዩ ሃይልና የፌደራል ፖሊሶችን በጋራ በአዲስ አበባ ለመጠቀም ሲባል፣ መስተዳድሩ የጸጥታ ጉዳዮችን ለጨፌ ኦሮምያም ጭምር ሪፖርት እንዲያደርግ ታዟል። የእቅዱ ዋና ነዳፊ የሆኑት የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አባይ ጸሃየ፣ ጸጥታን በተመለከተ የኦሮምያ ምክር ቤት ሪፖርት እንዲቀርብለት፣ የልማት ጉዳዮችን በተለይ መሬትን በተመለከተ ደግሞ የአዲስ …

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉምበርግ የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እንግሊዝ በኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመደጎም ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ያቋረጠችው፣ መንግስት መጪውን ምርጫ ተከትሎ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን ማሰሩንና መዋካቡን በመቀጠሉ ነው። የእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ጸሃፊ ጀስቲን ግሪኒንግ ፣ እንግሊዝ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑዋን ተከትሎ፣ ቀድም ብሎ ይሰጥ የነበረው የማህበራዊ …

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአለማቀፍ ታዛቢዎችና በኢትዮጵያውያን በቂ ትኩረት ያልተሰጠውን የግንቦት 16 ቀን 2007 ምርጫ ክርክር የሚሳተፉለትን መሪዎች ሲያፈላል የነበረው ኢህአዴግ፣ ለመጀመሪያው ዙር የክርክር መድረክ የሚሆኑትን ሰዎች ሲመርጥ፣ አቶ በረከት ራሳቸውን አግልለዋል። ኢህአዴግ 23 አመራሮችን ለክርክር በእቅድ የያዘ ቢሆንም፣ ከእነዚህ ወስጥ በመጀመሪያው ዙር መጣሪያውን ያለፉት አቶ  ሬዲዋን ሁሴን  እና አቶ ደሰታ …

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓም. በሚቆየው የአማራ ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በቀረበው  የግማሽ አመት ሪፖርት፣  ከየዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት በቀረቡት ጥያቄዎችንና ቅሬታዎች በክልሉ በተገነቡ የገጠር መንገዶች አሰራር ላይ ተገቢው …

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳው ውሃ ከ15 ቀን በላይ በመጥፋቱ ከጉረቤት ቀበሌያት እየተቀዳ የሚመጣው ንፅህናው ያልተጠበቀ አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 10 ብር እየተሸጠ ሲሆን ፣  ይህንኑ ውሃ በአህያ ጋሪ ከተማ ውስጥ ለመግዛት ነዋሪዎች ቀድመው ለመክፈል ይገደዳሉ ። አንዲት የጪኮ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችና በሰው ቤት የቀን ስራ ሰርታ የምትተዳደር ሴት  ” እቤቴ …

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠማቸው። ፕሬዚዳንቱ በተገኙበት ሆቴል የተገኙ ኢትዮጰያውያን ፦” ሰውዬው እጃቸው በደም የተጨማለቀ፣ የሱማሌ ክልል ወጣቶችን በመግደል በዘር ማጥፋት ክስ የተመሰረተባቸውና  እና ለዚህም  በዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ የሚገባ  ወንጀለኛ መሆናቸውን በማውሳት ከፍ ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል። በደረሰባቸው ድንገተኛ …

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች  የሚገኙ ግድግዳዎችና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በየእለቱ “ጭቆና በቃን! ነጸነትና ፍትህ እንፈልጋለን!  ለነጸነት ትግል ተነስ!” በሚሉ መፈክሮች አሸብርቀው መታየታቸው የተለመደ ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ  እነኚሁ  የፍትህና  የነጻነት ጥያቄዎች በመገበያያ የብር ኖቶች ላይ ሳይቀር በስፋት  እየተስተዋሉ መሆናቸው  የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሂደቱ በዚህ ከቀጠሉ  የብር ኖቶች በሙሉ …

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎቹ  ምሬታቸውን ለኢሳት ሲግልጹ፦” አቶ ሀይለማርያምን  ከልባችን አውጥተን ከጣልነው ቆይተናል” ብለዋል። በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን   የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ የሆነችው  የአረካ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት  በጠቅላላ የወላይታ ዞን  ነዋሪዎች በውሀ፣በመብራትና በስልክ ችግር  መማረር ከጀመሩ ረዥም ጊዜያት ሆኗቸዋል። በተለይ ካለፉት ሁለት ወራት  ወዲህ የአቶ ሀይለማርያም የትውልድ መንደር …

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመድ የመንግስትን ሪፖርት ዋቢ አድርጎ ባወጣው መግለጫ ዘንድሮ  በኢትዮጰያ 2.9 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። ከተረጅዎቹ መካከል 38 በመቶው  ከኦሮሚያ፣ 31 ከመቶው ደግሞ ከሶማሌ፣ 12 በመቶው ከትግራይ እና 6 በመቶው ካማራ ክልሎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል። ለተረጅዎቹ ድጋፍ ለማድረግ  386 ሚሊዮን ዶላር  እንደሚያስፈልግ ያመለከተው ተመድ፤ ይሁንና …

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን ሲመለምሉና  መንግሥትንና ተቋማቱን ሲሰልሉ  ተደርሶባቸዋል፣ እና  የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምሕት)  ቡድን ምልምሎች  ናቸው>>  ባላቸው ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሠረተ፡፡ <<የወንጀሉ ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር>> ተብለው  …

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢ ተቆርቋሪና የማህበረሰብ ቱሪዝም ኤክስፐርት  የሆነው ወጣት  ቢኒያም አድማሱ ሰሞኑን በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ  እንደተቀሰቀሰ መስማቱን ተከትሎ  ወደዚያው በማቅናት  እሳቱን  ለማጥፋት  ሲረባረብ ነው  በቃጠሎ ህይወቱ ያለፈው። ወጣት ቢኒያም ወደባሌ ብሄራዊ ፓርክ ያቀናው እንደሱ እሳቱን ለማጥፋት  ከዘመቱ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሰባሰብ ነበር። በስፍራው ደርሰው በጋራ ርብርብ በሚያደርጉበት ወቅት  …

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብራሪዎች ባለፉት 6 ወራት ከድሬዳዋ አየር ሃይል ግቢ ጠፍተው ተቃዋሚዎችን መቀላቀላቸውንና መሰደዳቸውን ተከትሎ ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ በቀሪዎቹ ላይ የዛቻና የማስፈራሪያ ንግግሮችን በማድረግ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል ። የአየር ሃይል ምንጮች እንደተናገሩት፦ጀነራሉ <<ከጠፉት የአየር ሃይል አባላት ጋር ግንኙነት ነበራቸው>>ያሏቸውንና  <<ሊጠፉ ሲሉ ተያዙ የተባሉ ሌሎች የአየር ሃይል አባላትን>>  ለቀሪዎቹ …

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ ማንነቱን በማያውቁት ሰው ድብደባ ተፈጸመባቸው። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ወደ ፍርድ ቤት እየሄዱ ሳሉ ሜክሲኮ አካባቢ ብሔራዊ አረቄ ፋብሪካ መታጠፊያ ላይ አንድ  እብድ የሚመስል ሰው  ተንደርድሮ ዐይናቸውን በቡጢ  ክፉኛ መቷቸዋል። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ ሆነው ለረዥም ጊዜ …

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ሲሉ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለአውሮፓ ህብረት መልእከት አስተላለፉ። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር  ይህን ያሉት የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ  ላይ ነው።  ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት  አምባሳደሮችና ተወካዮች በተገኙበት በዚህ …

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ ፓርቲ  አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ በመባላቸው  የሰባት ወር እስራት ተፈረደባቸው። የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት  ዛሬ መጋቢት 1 ቀን  2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት  በመድፈር በሰባት ወር እስራት እንዲቀጡ …

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆኑ የጋምቤላ አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን በየጊዜው እንደሚገደሉና የጸጥታው ሁኔታ እየተበላሸ መሆኑን በተለያዩ የመንግስትና የግል ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ገልጸዋል። መታሃር፣ ላሬ፣ ኢታንግ እንዲሁም ፑጊዶ በሚባሉ አካባቢዎች ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎች አብዛኛውን ጊዜ በግል ኩባንያዎች ተቀጥረው በሚሰሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው። እነዚህ ታጣቂ ሃይሎች የሚወስዱትን እርምጃ …

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረር ከተማ ካለፈው ሁለት ሳምንት ጀምሮ እንዳዲስ በተጀመረው አፈሳ በርካታ በቀን ስራ የሚተዳዳሩ ነዋሪዎች ታፍሰው ወደ አልታወቀ ስፍራ የተወሰዱ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ግን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ተወስደዋል ብሎዋል።  እሁድ እለት ደግሞ  በርካታ  አዲስ ምልምል ታዳጊዎች ደግሞ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ብር ሸለቆ ተወስደዋል። እድሜያቸው ከ12 እስከ 13 አመት የሚደርሱ …

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ደረጃ አንድ፣ ደረጃ ሁለት እየተባለ  እስከ አስር ደረጃ ድረስ የስራ ተቋራጭነት ፈቃድ የሚሰጥ ሲሆን ይህንን ፈቃድ ለማግኘት  እንደዶዘር፣ ግሬደር፣ እስካቭተርና ፒክ አፕ ያሉ መኪኖችን መያዝ በቅድመ ሁኔታነት የሚጠየቁ ቢሆንም፣  ሥራ ተቋራጮች እነዚህ ተሸከርካሪዎች እንዳሉዋቸው በማስመሰል ከትራንስፖርት ባለስልጣን አንዳንድ ሃላፊዎች ጋር እየተሻረኩና የጥቅም ትስስር እየፈጠሩ …

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሱዳን ትሪቢዩን የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ ከህገ ወጥ አሻጋሪዎቹ መክከል ሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል። እንደ ሱዳን ፖሊስ ገለጻ አደጋው የደረሰው ከካርቱም 79 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና አል-ባካ ተብላ በምትጠራው አካባቢ  ባለው “የሺሪያን  አል-ሺማጅ” የቀለበት መንገድ ላይ ነው። እስካሁን  ከተጎጆዎቹ መካከል 15ቱ …

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ የተከለለውን ቦታ 40 የሚሆኑ የምክር ቤት አባላትና ደጋፊዎቻቸው መከፋፈላቸው የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ፣ የካቲት 27 ጧት ላይ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ የከተማው ፖሊስ ጣቢያ ፣ መዘጋጃ ቤት፣ መስተዳድሩና የብአዴን ጽህፈት ቤት መስኮቶችና በሮች ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የመዘጋጃ ቤት …

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካርቱም ሱዳን ውስጥ ሲደረግ የነበረው ሶስቱ አገራት ድርድር በስኬት መጠናቀቁን የሶስቱም አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስታውቀዋል። የግብጽ የውሃ ሃብት ሚኒስትር  ስምምነቱ ግብጽ በግድቡ ላይ ያላትን ስጋት ያስወገደ ነው ብለዋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ካርቲ በሶስቱ አገራት መካከል ሙሉ ስምምነት መደረሱን ገልጸዋል። የተስማሙባቸውን መርሆዎች ለሶስቱን አገራት መሪዎች …

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር ነጻ አውጭ ድርጅቶች በአካባቢው እያደረሱት ያለው ተጽአኖ ያሰጋው መከላከያ፣ በአፋር የተለያዩ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው። ስማቸው ለደህንነት ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቁት ወላጆች በደርግ ጊዜ የቀረው አፈሳ በክልሉ እንደ አዲስ መጀመሩን ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች አፈና በመፍራት ጫካ መግባታቸውንም ነዋሪዎች አክለዋል። አርዱፍ፣ አፋር ጋድሌና የአፍዴራ ወጣቶች …

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢጋድ ሊቀመንበርነታቸው ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የደቡብ ሱዳንን መንግስትና ተቃዋሚውን ሃይል ለማቀራረብ ለወራት ሲደከምበት የነበረው የሰላም ድርድር ያለውጤት  ተበትኗል። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ያለፉትን 4 ቀናት በአዲስ አበባ ያሳለፉ ቢሆንም፣ መሰረታዊ በሚባሉት የስልጣን ክፍፍል፣ ፌደራሊዝም እንዲሁም በሰራዊት ውህደትላይ መግባባት ሳይችሉ ቀርተዋልአቶ ሃይለማርያም  ያለንን ሃይል ሁሉ …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የአረና ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል የመሰኖ ውሃ እንዳያጠጡ በመከልከላቸው፣ ሰብሎቻቸው እየደረቁ ነው። 12 አርሶ አደሮችን በመወከል ለኢሳት የተናገረው አቶ ህድሮም ሃይለስላሴ የተቃዋሚ አባላት ብቻ በመሆናችን አትክልቶቻችንን የመስኖ ውሃ እንዳያጠጡ፣ ከእነሱ መካከል ሁለቱ ብቻ …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞ የሸእቢያ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦህዴድ 25ኛ አመት የእዮቤልዩ በአሉን ድል ባለ ድግስ ለማክበር በማሰቡ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶችን ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ የድርጅቱ ካድሬዎች ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በመቀስቀስ ላይ ናቸው። የክልሉ ፕሬዚዳንት የካቲት 29 ቀን 2007  ዓም ባለሃብቶች በአሉን ስፖንሰር እንዲያደርጉ ለመጠየቅ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ስብሰባ ጠርተዋል። ድርጅቱ …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የሚገኘው ደን ካለፉት 3  ቀናት ጀምሮ በእሳት እየወደመ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የጸጥታ ሃይሎች እሳቱን ለማጥፋት በመረባረብ ላይ ናቸው። ይህን መረጃ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምን ያክል ስፋት ያለው ደን እንደወደመ ለማወቅ አልተቻለም። በባሌ ዞን በወረዳ ሼዳ ቀበሌ አካባቢም …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአባይ  ወንዝ ላይ የተሰራዉ 108 ሜትር ርዝመት እና አንድ ነጥብ ስድስት  ሜትር ስፋት ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ  በሃገሪቱ ብቸኛዉ የተንጠልጣይ  ድልድይ በመስራት በሚታወቀው  ሄልቬታስ ሲዊዝ ኢንተርኮኦፕሬሽን በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በይፋ ተመርቆ ስራ ቢጀምርም፣ በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ባለሙያዎች ድልድዩ የጥራት ችግር እንዳለበት መናገራቸው …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ  ሰራዊት  ከፍተኛ  መኮንኖች  እና  መንግስት  ከፍተኛ  አመራሮች  በተገኙበት  በተደረገው  የምስጋና  ሲመፖዝየም  በከተማዋ  ከሚገኙ  ክፍለ  ከተማዎች  የተመረጡ  የገዢው  ፓርቲ  አባላትና  አቀንቃኞች እንዲሁም ከየመምርያው  የተወከሉ አባላት በተገኙበት መከላከያ ሰራዊቱ ለሃገሪቱ ዘብ የቆመ፣ በልማቱ ተሳታፊና ሁለንተናዊነቱን በማንሳት መወድሰ- መከላከያ ሰራዊት ሲደረግ ውሎአል። በዚህ የሰራዊቱን አመራሮች የማድነቅ ስነስርዓት ላይ ንግግራቸው …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም በሱዳናዊ ሹፌር በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የተፈጸመባት ኢትዮጵያዊት ወጣት ማረፉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወጣቷ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ተወጋግታ መሞቱዋን የገለጹት የወረታ ነዋሪዎች፣ ሹፌሩ በቁጥጥር ስር ውሎአል ቢባልም በትክክል ስላለበት ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ጭኖ ይጓዝ የነበረውን መኪና …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከሳሽ ኣቃቤ  እና  ህግ በተከሳሽ አቶ ኣስገደ ገ/ሥላሴ መካከል ሲደረግ በነበረው ክርክር  ለምስክርነት የተጠሩት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊቀርቡ ባለመቻካቸው  በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ  ቢታዘዝም፤  ባለስልጣናቱ  ከለመዱት ምቹ ህይወት አኳያ ማቅረብ ሳይቻል ቀረ። የህወሀት የደህንነት ሰራተኛው ብስራት አማረ  የመሰረተባቸውን ክስ  ተከትሎ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲከራከሩ  የቆዩት የቀድሞው የህወሀት ታጋይና …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ የዙሪክ ነዋሪ የሆኑት አክቲቪስት  ፊዮሬላ ሮማኖ ለኢሳት እንደገለጹት  ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ቀጠሮ አስይዘው ከሚኖሩበት ዙሪክ ኤምባሲው ወደሚገኝበት ጀኔቫ የ3 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ቢሄዱም፣ የኤምባሲ ስራተኞቹ በአካል ሲያዩዋቸው በተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚሳተፉ ስለለዩዋቸው አገልግሎቱን  ሳይሰጡ መልሰዋቸዋል። ኤምባሲው እንደደረሱ ጎይቶም በሚባል ሰራተኛ የተሰጣቸውን ፎርም ከሞሉና ፎቶግራቸውን ከሰጡ በሁዋላ በስዊዘርላንድ ለምን …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀፍታ ሑመራ ወረዳ  በረኸት  ከተማ  ነዋሪ የሆኑት ቄስ ሕሉፍ ኸሕሳይ የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ዘግናኝ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የወጣ መረጃ አመለከተ። እንደ መረጃው ከሆነ  ቄስ ህሉፍ  በደረሰባቸው ዘግናኝ ድብደባ  በህይወትና በሞት መካከል የሚገኙ ሲሆን፤ ለድብኢደባቸው ምክንያቱ  የአረና አባል መሆናቸው ብቻ ነው። የካቲት 17 ቀን 2007ዓመተ …

የካቲት ፳፬(ሃያአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጊቱ የተፈጸመው  ማክሰኞ የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም ሲሆን አንድ የሱዳን ታርጋ ያለው ፣ በሱዳናዊ ሹፌር የሚሽከረከር ማዳበሪያ ያጫነ ከባድ መኪና  ከሱዳን ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ ነው። መኪናው እንፍራዝ እየተበላ በሚጠራ አነስተኛ ከተማ ላይ ሲደርስ አንዲት መኪና በመጠበቅ ላይ የነበረች ኢትዮጵያዊት ወጣት ሹፌሩን ትብብር ጠይቃው  ትሳፈራለች።  ምክንያቱ በውል …

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ፣ ኤፍ ኤም 96.3፣ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ ያቀረባቸውን መልእክቶች እንዲለውጥ፣ ካልለወጠ ግን እንደማያስተላልፍ ገለጸ። ጣቢያው እንዲወጡ ከጠየቃቸው መልእክቶች መካከል ‹‹ሀገራችን ዛሬ በቀሪው ዓለም የምትታወቀው በእርስ በርስ ጦርነት ነው›› የሚለው የሚገኝበት ሲሆን፣ መልእክቱ ለአመጽና ለሁከት የሚያጋልጥ ነው የሚል ምክንያት …

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞ የደርግ ወታደሮችን በማሰባሰብ  በህወሓት በጎ ፈቃድ የተመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተመሠረተበትን 25 ዓመት በድምቀት ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳባ ደበሌ  በሰጡት መግለጫ ኦህዴድ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ከመጋቢት 1 እሰከ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሃግብሮች …

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅዱስ ጊዮርጊስ እና  የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ  ቡድኖችን  ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡ አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ …