በሻውራ ከተማ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተከስቷል
መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሻውራ ከተማ የከተማዋ ነዋሪዎች ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ውሃ በማጣታቸው መቸገራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ለመግዛት ተገደናል የሚሉት ነዋሪዎች ምክንያቱም ሙስና ነው ይላሉ። የወረዳው መስተዳደር 300 ሺ ብር የተገዛውን ጄኔረተር 800 ሺ ብር እንደተገዛ አድርጎ ማቅረቡን የሚናገሩት …