ገዢው ፓርቲ ህዝቡ በቡድን ድምጽ እንዲሰጥ እያዘጋጀ ነው
ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግንቦት አጋማሽ ሊደረግ በታሰበው ምርጫ ላይ ገዢው ፓርቲ በቡድን ድምጽ የሚሰጡ ዜጎችን በማደራጀት ላይ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል። ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የሚደረገው ገዢው ፓርቲ አንድ ለአምስት እያለ በሚጠራው የአፈና ስርአት ውስጥ ሆነው ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በድምጽ መስጫው ቀን በአንድ ለአምስት የተደራጁትን ሰዎች በአንድ ላይ …