ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ባወጡት ሪፖርት በሲቲ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በተከሰተው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ በጎችና ፍየሎች ሲያልቁ ነዋሪዎችም እየተሰደዱ ነው። በረሃቡ ምክንያት በሃዲጋላ ወረዳ ጉርጉር ቀበሌ በጎች የሌሎችን በጎች ቆዳ ሲበሉ መታየታቸውን በስእል የተደገፈው ሪፖርት ያሳያል። አይሺያ፣ ሃድሃጋላ፣ ከፊል ሽንሌ፣ ከፊል ደምበል፣ …

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መካከል የስኳር ፕሮጀክቶች በዋነኛነት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እንዳልተሳኩ ከስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በሰኔ ወር 2007 መጨረሻ የሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት መርሃግብሩ ከተያዙት ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ለፕሮጀክቶቹ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ ሊሰጡ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት …

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት አይኤስን ለማውገዝ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የተባሉትና በወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት ተከሳሾች ላይ መደበኛ ክስ ተከፈተ። በዚህም መሰረት የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛና የአንድነት አባል የነበረው ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ በሌሎች 18 ተከሳሾች ላይ የፌደራል ዐቃቤ ህግ ክስ …

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እየተዋከቡ፣ እየታሰሩና ደብደባም እየተፈጸመባቸው መሆኑን በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች አንድ ጊዜ የቡና ሌላ ጊዜ የእድር እያሉ በተለይም እናቶችን እየሰበሰቡ ኢህአዴግን እንዲመርጡ፣ ልጆቻቸውንም አመጽ እንዳያስነሱ እንዲመክሩ ለማግባባት ይጥራሉ። መራጮች በኢህአዴግ ካድሬዎች የቅስቀሳ መንገድ …

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ አካባቢ ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል ። በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማጣታቸውን የሚናገሩት የወረዳው ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጥያቄዎችን ባነሱ ነዋሪዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል ። በተለይ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሚካሄድውን ምርጫ ጋር በተያያዘ ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት እማኞች፥ ከተገደሉት …

በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስቲያንናት እንዲሁም የተለያዩ የሲቪል ድርጅቶች በቅርቡ በየመን፥ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር እሁድ እለት በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የመታሰቢያ ዝግጅቶችን አካሄዱ። ነዋሪነታቸው በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ በርካታ ኢትዮጵያዊን በታደሙበት በዚህ ዝግጅት፥ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሟች ኢትዮጵያዊያንን አስመልክቶ ያስተላለፉት የሀዘን መልክት ተነቧል። ልዪ የጸሎትና …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተጠናክሮ በደረሰው ሪፖረት ህዝቡ “እኛ ኢቲቪን (ኢቢሲን) አይተን አናውቅም ፤ ለውሸት ጣቢያ ፈፅሞ ክፍያ አንፈፅምም ፤ በአይናችን ያየነውን ለሚክድ ሚዲያ እኛ ምንም ድጋፍ አናደርግም፡፡ እንደዚህ የሚባል ጣቢያ አለ እንዴ ፤ ኢቲቪ የሚባል ጣቢያ መኖሩን አናውቅም ነበር ” የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ፣ አንዳንዶች ደግሞ “እኛ ከኢሳት …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማንኛውም አማራጭ ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸውን ውይይት መጀመራቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ውይይቱን የጀመሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን)፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘጋቢያችን በላከችው ሪፖርት የገዢው መንግስት ካድሬዎች በየመንደሩ በመዞር የሚደርጉት የምርጫ እንቅስቃሴ የነዋሪዎችን ነጻነት ከማሳጣቱ በተጨማሪ፣ ኢህአዴግ በሚጠራው የመንደር ስብሰባዎች የሚቀር ሰው የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ተብሎ ይመዘገባል። የገዢው ፓርቲ አባላትና የቀበሌ አመራሮች በየሰፈሩ በሚያደርጉት ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ ባለሃብቶችን ያለ ፈቃዳቸው ለዕለቱ የሚስፈልገውን ለቡና፤ዳቦ እና ቆሎ ዝግጅት የሚውል …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም በሰልፉ ወቅት ከተያዘ በኋላ በ25 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ እንደገና የታሰረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር …

በጋምቤላና ደቡብ ክልል ድንበር አካባቢ የሪ በምትባል ቀበሌ 7 ሰዎች በተገደሉ ማግስት ሌሎች 5 ሰዎች ደግሞ በቴፒ ከተማ እንድሪስ ቀበሌ ውስጥ ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ በጥይት ተደብድበው መሞታቸውን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሟቾቹ መካከል አባትና ልጅ ይገኙበታል። ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ ገዳዮቹ ፖሊሶች ናቸው። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሰዎቹ ይተገደሉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ያስጠጋሉ፣ …

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲዊ አንድነት መድረክ ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም በጃንሜዳ የተጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በህዝቡ በኩል በተለይ ወጣቱ መንቀሳቀሱን ይሁን እንጅ ብዙ ቦታዎች ላይ የምርጫ ሜዳው መዘጋቱን ገልጸዋል። ህዝቡ በስሜት ስብሰባዎችን መሳተፉን የገለጹት ዶ/ር መረራ ፣ በምርጫው መቀመጫ ባይገኝ የህዝቡን ትግል ወደ አንድ እርምጃ ለመውሰድ በሚደረገው ሙከራ በብዙ ቦታዎች …

ፕሬዚዳንት ኑኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ለመመረጥ መወሰናቸውን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ መፈንቅለመንግስት ከተቀየረ በሁዋላ፣ አገሪቱ በምን ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ዋና ዋና የሚባሉትን ተቋማት በተለይም የሬዲዮ ጣቢያ፣ አየር መንገዱንና ቤተመንግስቱን በመቆጣጠር መፈንቅለ መንግስቱ እንደከሸፈ ቢያስታውቁም፣ መፈንቅለመንግስቱን የሚደግፉ ሃኢሎች በበኩላቸው፣ ተቋማቱ በእነርሱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ እየገለጹ ናቸው። መፈንቅለመንግስቱ ያልተሳካ መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች …

ጁባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ በዩኒቲ ግዛት የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት ጥቃት በሲቪሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ተቃዋሚዎች አጽፋዊ እርምጃ በመውሰድ ጦርነቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ መግለጫው ጠይቋል። የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ የሚፈናቀሉ ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥር ጨምሯል። እስካሁን ባለው መረጃ ከ300 ሺ ያላነሱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው …

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ አገዛዙን ይቃወሙ ይሆናል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በገፍ እየተያዙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ወጣቶችም ከእስር ለማምለጥ መሸሸጋቸውን ለኢሳት እየገለጹ ነው። በተለያዩ ክልሎች የገዢው ፓርቲ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶች የሚታሰሩት ከምርጫው ጋር በተያያዘ ህዝቡን ለአመጽ ያነሳሳሉ በሚል ነው። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መሪ …

Desalegn Hailemariam
ኢሳት ዜና:- ጠ/ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በሙሉ ሲያስገመግሙ ከከረሙ በሁዋላ በመጨረሻ ራሳቸው 15 ሰአታት በፈጀ ግምገማ ተገምግመዋል። አብዛኞቹ በአቶ ሃይለማርያም የስራ ችሎታና አመራር ላይ ዘለፋ ቀረሽ ሂስ አቅርበውባቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም የቀረበባቸውን ሂስ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው ግምገማው ረጅም ጊዜ እንዲወስድ አድርጓል። ግምገማው ከምርጫው በሁዋላ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ባለስልጣናትን ለመለየት እና ግድፈታቸውን አርመው ሰርተው እንዲጠብቁ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

አቶ ሃይለማርያም ከህወሃቶቹ ከአቶ አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋና አስመላሽ ወልደስላሴ የሰላ ትችት ሲቀርብባቸው፣ ከራሳቸው የደህዴን አባላት ከሆኑት ከአቶ ሬድዋን ሁሴንና ሙፈሪያት ከሚልም ዘለፋ ቀረሽ ትችት አስተናግደዋል። አብዛኞቹ ብአዴኖች፣ አቶ በረከት ሳይቀሩ የአቶ ሃይለማርያምን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ አስገብተዋል። በመጠኑም ቢሆን የራሩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብቻ ናቸው።

አቶ ሃይለማርያም እንቅስቃሴያቸውንና የሌሎችን ሰዎች እንቅስቃሴዎች የሚቆጣጠሩ የስለላ ካሜራዎች እንዳይተከሉ፣ በጽህፈት ቤታቸው ያለውም እንዲነሳ ማድረጋቸው ከደህንነት ሃይሉ ጋር አጋጭቷቸው እንደቆየና ውዝግቡ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑ ተወስቷል።

አቶ ሃይለማርያም አንዳንድ መልሶችን ሲሰጡ እንባ ይተናናቃቸው ነበር። በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ደግሞ በእልህና በወኔ ተሟግተዋል። አቶ ስብሃት ነጋ በአቶ ሃይለማርያም ላይ ለሰነዘሩት ትችት፣ አቶ ሃይለማርያም “ስብሃት በጣም ይጮሃል፣ እንዳሞራ ሁሉ ይዞረኛል፣ እዚህ ሳወያይም ይጮሃል፣ አለቃ መሆን ችግር ነው ብየ ዝም አልኩ። ንግግር ከመልክ ያምራል ይባላልና ያሳሳትኩት ነገር ካለ አርማለሁ። በአባባል ክፍተት ካለ ይቅርታ” በማለት መልሰዋል።

የግምገማውን ዝርዝር ሪፖርት በነገው ዘገባ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እናወዳለን።

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)፣ በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር ወረዳ ዲመካ ከተማና አካባቢው ከጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ ግጭት በ7 ሰዎች የሞትና በ9 ሰዎች የመቁሰል አደጋ መድረሱን በጥናቱ አረጋግጧል። ሰመጉ ባለሙያዎቹን በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማ እንዲገኙ በማድረግ …

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ሳምንታት በውዴታና በግዴታ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ  ወጣቶች አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸውን አምለጠው የመጡ ወጣቶች ለኢሳት ተናግረዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ወጣት “በመጀመሪያ የወረዳው ባለስልጣናት ለስብሰባ ጠርተውን መንጃ ፈቃድና ልዩ ልዩ ስልጠና ስለምንሰጥ ከነገ ጀምሮ ተነሱ አሉን። እኔና 50 የምንሆን ጓደኞቼ በማግስቱ …

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በተወሰኑ የፊደራል ፖሊስ አባላትና እና በማረሚያ ቤቶች ጠባቂዎች ላይ በተካሄደ ድንገተኛ ማጣራት፣ በ18 የፀጥታ አባላት ስልኮች ላይ በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም  ፎቶዎች መገኝታቸውን የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። የደህንነት ሃይሉ ከባለቤቱ ፈቃድ ውጭ ስልክ የመጥለፍ ፤ የኢንተርኔት አካውንት በመስበር …

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ መብራት እየተቆራረጠ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በህዝቡ ጥያቄ የተወጠሩት የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  ሃላፊ ሠራተኞቻቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ለመብራት መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ ምግባረ ብልሹ ሠራተኞቻቸው መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላ እና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ከተሞች የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ እየተበላሸ መሄዱን ተከትሎ  ዜጎች እየተፈናቀሉና እየተገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከሁለት ቀን በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በጎደሬ ወረዳ በየሪ ቀበሌ በፈጸሙት ጥቃት 6 ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷል። ሌሎች ወገኖች ደግሞ የማቾች ቁጥር 7 …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅማ ዩኒቨርስቲ ሰሞኑ በተደረገ አውደጥናት ላይ ፣ በየዓመቱ በየጊዜው የሚቀያየረው የትምህርት ፖሊሲ  ርእይ ያለው ወጣት እንዳይፈጠር ማድረጉ ተገልጿል ፡፡ ሀገሪቱ  ወጥ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ ይዛ ባለመማራቷ ችግሩ መፈጠሩንም ምሁራን ተናግረዋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ማምጣት የቻሉ ብዙ ተማሪዎች በምደባ  ከፍላጐታቸው የራቀ ትምህርት እንዲያጠኑ …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ ላይ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ስድስትወርእንደተፈረደበት ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጋዜጣው እንደሚለው ግንቦት 3/2007 ዓ.ምቄራየመጀመሪያ ፍርድቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል በቀረበበትክስ  የስድስት ወር እስር ተፈርዶበታል፡፡ አቶስንታየሁመቃወሚያና …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በሲሚንቶ እጥረት ግንባታዎች እንዲቋረጡ መደረጉን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችና በግንባታ ላይ የሚገኙ የህብረተሰቡ ክፍሎች ለዘጋቢያችን አስታውቀዋል፡፡ ችግሩ የህወሃቱ ንብረት በሆነው መሰቦ ስሚንቶና የሼክ አላሙዲን ንብረት በሆነው ደርባን ስሚንቶ መካከል ባለው ውዝግብ የተፈጠረ ነው ይላሉ ነጋዴዎች።  በዚህም የተነሳ ህብረተሰቡ ለአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከ80 እስከ 100 …

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ ” ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ” ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት ጠባቂዎች ጥብቅ ፍተሻና …

በሃገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ የዶላር እጥረት አስመጪና ላኪዎችን ማማረሩን ዘጋቢያችን ምንጮቹች ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ የላከው ዜና ያመለክታል። የቡና ኤክስፖርት ከቆመ ወራት ተቆጥረዋል፣ በሃገሪቱ ያሉ ባንኮች ዶላር ሽያጭ አቁመዋል የሚለው ዘጋቢያችን፣ ከዲያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ዶላር ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አዘጋጅቷል ብለአል። በአስመጪና ላኪ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ዶላር ማገኘት ያልቻሉበት መንገድ አልተገለጸላቸውም። ይሁን እንጅ የቡና …

በተራዘመ የፍርድ ሄደት የሚሰቃዩት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ፣ የመጨረሻ ብይን ሚያዚያ 30 እንደሚሰጥ አስቀድሞ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ የብይኑ ቀን እንደገና ተራዝሟል። የመራዘሙ ዜና አስቀድሞ በኢሳትና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተዘገበ በመሆኑ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስገራሚ አላደረገውም። አገሪቱን የሚመራት የደህንነት መስሪያ ቤት ከምርጫው በፊት ምንም አይነት ውሳኔ እንዳይሰጥ ትእዛዝ አስተላልፎአል። በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ …

በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኢህአዴግ ካድሬዎች እያደረጉት ያለውን የምርጫ ቅስቀሳና የካርድ እደላ የታዘበው ዘጋቢያችን የምርጫው ሂደት አስቂኝ ሆኗል ብሎአል። በከምሴ፣ ደብረብርሃን፣ ደብደረማርቆስና ሌሎችም ቦታዎች ካርድ ያለወጡ ሰዎች ኢህአዴግን እንደሚመርጡ ካርድ እየተሰጣቸው ነው። በአንድ ለአምስት፣ በአንድ ለአስር እንዲሁም በቡና ጠጡ መስተንግዶ ዜጎች በቡድን እንዲመርጡ እየተደራጁ ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች የቅስቀሳና የማደራጀት ስራ እየሰሩ ነው። ወሎ፣ ድብረብርሃን፣ ጅማና …

በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣ አምና በሚያዚያ ወር ከ79 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአምቦና አካባቢዋ ከተገደሉ በሁዋላ፣ ባለፉት 10 ቀናት ደግሞ 50 የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መያዛቸውን ገልጿል፤፡ ከ20 በላይ ወጣቶች በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸው በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። ድርጅቱ ባሰባሰበው መረጃ በእስር ላይ የሚገኙ 20 ተማሪዎችን ስም ይፋ አድርጓል። ወጣቶቹ …

ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ፣ እስካሁን ባለው መረጃ 9 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል። ሟቾቹ ለገሃሪ እንደገበሬ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። የ9 ሰዎች አስከሬን ተፈልጎ መገኘቱን ምንጮች ገልጸዋል። ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም በደረሰ ጎርፍ በርካታ ነዋሪዎቿን ማጣቷ ይታወቃል።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሳውድ አረቢያዊ የሆኑት ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን በሸራተን አዲስ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በስፍራው የተገኙትን የመንግስት ጋዜጠኞችና አንዳንድ የግል ሚዲያ ሃላፊዎችን ወቅሰዋል። ሼክ አላሙዲን በአሜሪካና በአውሮፓ የደሀ መሬት እየወሰዱ ነው እያሉ ስማችንን የሚያጠፉ ስራፈት ሚዲያዎች አሉ ያሉ ሲሆን፣ እናንተም የተባለው ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብላችሁ፣ መርምራችሁ ለህዝቡ ማቅረብ ነበረባችሁ በማለት ለዘገባ የተላኩ …

በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በማካሄድ ላይ ባለው 56ኛው አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ህዝቦች መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም ባቀረበው ጽሁፍ ፣ ነጻነትን በማፈን የአለም ሻምፒዮን ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዳ መሆኗን ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚባለውና የሚደረገው የተለያየ ነው የሚለው ድርጅቱ ፣ የአገሪቱ ህዝብ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን እንዳያገኝ መታፈኑን ገልጿል። በአገሪቱ አስገድዶ …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ሲሆኑ እስካሁን በዶክተሮች ለመጎብኘት አልቻሉም። አያያያዛቸው የከፋ መሆኑን በማስመልከት የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መጻፉንም ምንጮቻችን ገልጸዋል። አቶ አንዳርጋቸው ያለፉትን ተከታታይ ወራት ጸሃይ የሚባል ነገር ሳያዩ ጨለማ ቤት …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተይዘው በወረዳ 5 ቀበሌ 08/09 በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ወጣቶች ዛሬ ጧት ላይ በሶስት አይሲዙ መኪኖች ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ በቅርቡ በአዲስ አበባ የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ ከየስፍራው የተሰባሰቡ ሲሆን፣ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ በሚል …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክትል የውጭ ጉዳይ ሃላፊዋ ውንዲ ሸርማን በቅርቡ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት በመንግስት ሚዲያ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲና ምርጫ አድንቀው መናገራቸው ከየአቅጣጫው ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ዋሽንግተን ፖስት የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ በርእሰ አንቀጹ ወንዲ ሽርማንን የተቸ ሲሆን፣ ባለስልጣኗም ጋዜጣው በተሳሳተ መንገድ እንደተረዳቸውና ትችቱ ተገቢ አለመሆኑን በጽሁፍ መልስ ሰጥተዋል። ባለስልጣኗ ኢትዮጵያ አስቸጋሪ በሆነበት …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሬውተርስ የግብጽ መንግስታዊ  የዜና ማሰራጫን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤ ሊቢያ ውስጥ ታግተው የነበሩና በግብጽ ጦር ጥረት ከታገቱበት የተለቀቁ 27 ኢትዮጰያውያን ዛሬ ሀሙስ ካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ ገብተዋል። ኢትዮጰያውያኑ በግብጽ አውሮፕላን ተጉዘው ካይሮ ሲደርሱ በግብጽ ፕሬዚዳንት በአብደል ፋታህ አል-ሲሲ እና በሌሎች ከፍተኛ የግብጽ ባለስልጣናት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤የአቀባበል ሥነ-ስር ዓቱ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በቅርቡ በዩቴልሳት ስርጭቱን በአዲስ መልክ ማሰራጨት ቢጀምርም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምክንያቱ በውል ባልተወቀ ሁኔታ ስርጭቱ ተቋርጧል። እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቱ እንዲገለጽላቸው  ለሚያቀርቡት ጥያቄ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቓል። የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የኢሳትን ስርጭት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) የአሁኑ ሰመጉ ሚያዚያ 26 ቀን 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ በአዋሳና አዲስ አበባ በሚገኙ የድርጅቱ ፅህፈት ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል። መንግስት በተለያዩ ወቅቶች ላይ በድርጅቱ ላይ አፍራሽ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የጠቀሰው ሰመጉ፣ ሚያዚያ 24 ቀን 2004ዓም የሰመጉ የሃዋሳ ቅርንጫፍ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ቢያቅድም ፣ ማካሄድ እንደማይችል ተነግሮታል። አስተዳደሩ ‹‹መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በርካታ የተከማዋ ነዋሪ የሚተላለፍበት እና የከተማው ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነው” በማለት ጥያቄውን አለመቀበሉን ገልጿል። መንግስት በቅርቡ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ብቻ በዲዛይንና በሙስና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመባከኑ፣ ግብር ከፋዩ ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረጋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት በፌደራል የውሃ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት አማካሪነት እና በፌደራል ውሃ ስራዎች ቁጥጥር ድርጅት ተቋራጭነት የግንባታ ስራው እየተካሄደው ባለው የርብ መስኖና ግድብ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳሚ ሹክሪ ወደ ጁባ በማቅናት ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የሚመክሩ ሲሆን፣ ወደ ኤርትራም በማቅናት በሽበርተኝነት፣ እና በአካባቢው ባሉ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ የግብጹ አል ሃራም ዘግቧል። ጉብኝቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ መንግስት ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመራቸውን ባስታውቁ ማግስት እንዲሁም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የአባይን ግድብ በተመለከተ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤደንን ለመያዝ በሃውቲ ሚሊሺያዎችና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሃዲ መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን፣ 80 ሲቪሎች በጦርነቱ መሃል መገደላቸው ተዘግቧል። የሃውቲ ሚሊሺያዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ታማኞችና በአረብ አገራት ጥምረት የአየር ሃይል ጥቃት የተነሳ እስካሁን የኤደንን ከተማ ለመያዝ አልቻሉም።የከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም የመተማ ከተማ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በሄዱ ቤት አፍራሾችና የወረዳው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም፣ የፌደራል ፖሊሶች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ 2 ነዋሪዎች በጥይት ተመትተው ሲገደሉ፣ 3 ደግሞ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ቆስለዋል። ከ50 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ለመዘከርና ቁጣቸውን ለመግለጽ ገዢው ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወጣቶች መንግስትን ሰድባችሁዋል በሚል ታፍሰው ከታሰሩ በሁዋላ፣ “ተቃውሞውን ያስነሱት በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ናቸው” ብላችሁ ካልመሰከራችሁ አትለቀቁም መባላቸውን የእስረኞች ቤተሰቦች ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ወጣቶች ማታ …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 74 ኛ አመት በአዲስ አበባ ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት ተከብሯል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ሽንፈትን የተከናነበው ጣሊያን፣  ከ40 አመት በሁዋላ ራሱን በዘመናዊ መሳሪያ፣ በገንዘብና በሰው ሀይል አደራጅቶ ኢትዮጵያን ቢወርም፣ አባት አርበኞች ለ5 አመታት በዱር በገደሉ ባደረጉት ተጋድሎ፣ የፋሽስት ሙሶሎኒን ጦር ድል …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ” የኢንዱስትሪውን  ልማት በተሳለጠ መንገድ ይዘን በመጓዝ የአምስት አመቱን ዕቅድ ለማጠናቀቅ  በስኬት ጎዳና ላይ ነኝ ” በሚል  የገዢው መንግስት ቢናገርም፤ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች በርካታ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በተካሄደው የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት  ከከፍተኛ ባለሃብቶች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ፣ ባለሃብቶች  እንደገለጹት …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ ሜይ 2፣ 2015 ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶና ታዋቂው ጸሃፊ እና ፖለቲካ ተንታኝ አቶ የሱፍ ያሲን፣ አገራችን ከገባችበት ችግር መላቀቅ የምትችለው  በአንድነት በመነሳት መሆኑን ተናግረዋል። አቶ የሱፍ ገዢው ፓርቲ ባመጣው የፌደራል ስርአት ሳንጣላ ተራርቀናል …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን ለመዘከር የወጣው ህዝብ ተቃውሞውን ወደ ኢህአዴግ መንግስት ካዞረ በሁዋላ፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ያስነሳው በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገለው ሰማያዊ ፓርቲ ነው በማለት የከፈተው ሰፊና አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ የህዝቡን አመለካከት ሊቀይር አለመቻሉ ከፍተኛ ካድሬዎችን ስጋት ላይ ጥሎአቸዋል፡፡ በመስቀል አደባባይ የታየውን ህዝባዊ ቁጣ  ሰማያዊ …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ታህሳስ ወር አርበኞች ግንቦት7ትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ መንገድ ላይ ተይዘዋል ባላቸው እሰረኞች ላይ ለደረጃ ምስክርነት አብረው ከታሰሩት መካከል እያሰለጠ ነው። አንዳንዶች ፖሊስ ራሱ ያዘጋጀውን ቃል በፍርድ ቤት ተገኝተው የሚሉ ከሆነ ከእስር እንደሚፈቱ ፣  ለመመስከር ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ እድሜ ልካቸውን በእስር ላይ እንደሚቆዩ እንደተነገራቸው …