ስቅለትከሆሳዕና እስከ ማዕዶት

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው። የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው።” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው። “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሶስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል “ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው” የከተማው ኮሙዩኒኬሽን “ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት የተቧደኑ ወጣቶች፣ ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ፤ ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት […]

የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ለማድረግ ላሰገባዉ የማሳወቂያ ደብዳቤ ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምላሽ እንዳገኝ ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ። የአስተዳደሩ ደብዳቤ፣ ሰልፉን በታሰበው ሚያዚያ 19 ቀን፣ ማድረግ እንደማይቻልና ለሌላ ቀን እንዲያስተላልፈው የሚጠይቅ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ ግን፣ ለሰልፉ መራዘም የቀረቡት ምክንያቶች በቂ አይደሉም በሚል፣ ቀኑን እንደማይለወጥ፣ ባስገባው ሁለተኛ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አሳዉቋል። የሰማያዊ ፓርቲ በላከው ሁለተኛ ደብዳቤ፣ […]

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

የ1994 የሩዋንዳ የጭፍጨፋ እና የእልቂት ጸጸት በ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰማይ ላይ እያንዣበበ ነው!

ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ ህዝብ እርስ በእርስ የተራረደበትን 20ኛውን ዓመት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መጥፎ ገጽታ ለማስታወስ የሀዘን ሳምንት አውጆ ድርጊቱን በመራር ሀዘን ዘክሮታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከአንድ ሣምንት በኋላ ወደግብፅ የሚያደርጉት ጉዞ በህዳሴ ግድብ ላይ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ አቡነ ማትያስ አስታወቁ።

ግድቡን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ያለው አስተሳሰብ ግልፅ እና አብረን እንጠቀም መሆኑን የተናገሩት አባ ማትያስ ርዕሱ ከተነሳ ምላሽ እንደሚሰጡ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

ኬንያ ውስጥ ሰሞኑን በስደተኞችና ፍልሰተኛ ነዋሪዎች ላይ እየካሄደ ያለው ፍተሻ፣ የቤት ለቤት አሰሳና የጅምላ እሥራት የፈጠረው የውጥረት ድባብ የሰብዓዊ መብቶች ጥያቄዎችን እያስነሣ ነው፡፡

ቪኦኤ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለና ዘገባዎችንም እያወጣ ነው፡፡

ከኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች መካከል እያነጋገርን ነው፡፡

የኬንያ ፖሊስ ያለህጋዊ ፈቃድ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የውጭ ሀገር ስደተኞችን ዒላማ ባደረገው ዘመቻችው ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን መርምረናል፥ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሰዎችን ልናስወጣ ነው ሲል አስታውቋል።

ለሰብዓዊ መብቶች የሚሟገቱ ቡድኖች እና ኬንያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ፖሊሶች ያዋክቡናል፥ ጉቦ ይጠይቁናል ፥ በጎሣችን ምክንያት የዘመቻው ዒላማ እየተደረግን ነው ሲሉ አማርረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ዘንድሮ የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ በተመሳሳይ ቀን ይከበራል። የአይሁዳውያን ፋሲካም በትንሣኤ ቀን ይውላል። የትንሣኤ በዓል ከሐይማኖታዊ ዳራው ባሻገር እንደየሀገሩና የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችም አሉት። በተለይ የዶሮ እንቁላል ሀገር ቤትም ሆነ እዚህ ጀርመን በትንሣኤ በዓል ልዩ ስፍራ ይሰጠዋል።

ይህ የአራትዮሹ ንግግር ለዩክሬን ቀውስ ምን ዓይነት መፍትሄ እንደሚያስገኝ ከወዲሁ መገመት ቢያዳግትም ቢያንስ ዩክሬንና ሩስያን የዩክሬን ቀውስ ከተባባሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ላይ እንዲወያዩ በማድረጉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ።

የጀርመን መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠሪ ክርስቶፍ ሽትሬሰር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በተለይ ግጭቶች እየተባባሱ በሚሄዱባቸው አካባቢዎች ህዝቡን በሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከዚያም አልፎ ተፋላሚ ወገኖችን ቢቻል በሰላማዊ መንገድ አለያም በኋይል ማስቆም እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንዳገኘ መዘገቡ ይታወቃል። አንድነት ሰልፉን መጋቢት 28 ቀን ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር በተባለው ቀን እውቅና ባለመስጠቱ፣ የተለያዩ ዝግጅቶ በመኖራቸውና የአመት በዓላትም ጊዜ በመሆኑ፣ ወደ ሚያዚይ 26 መሸጋገሩን የአመራር አባልቱ ይገልጻሉ። በዚህ ሂደት ከአስተዳደሩ ጋር በርካታ የደብዳቤ ልዉዉጦች የተደረጉ ሲሆን፣ […]

የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንደገኘ መዘገቡ ይታወቃል። በተመሳሳይ ሁኔተ የሰማይዊ ፓርቲ ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዚያ 19 ቀን በጃን ሜዳ ሰልፍ መጥራቱን ገልጿል። አስፈላጊዉን የማሳወቂያ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ እንዳሰገቡ ሰማያዊቾ ቢገልጹም፣ በተባለው ቀን ከአስተዳደሩ እውቅና ይሰጣቸው አይሰጣቸው እስከ አሁን የተወቀ ነገር የለም። ሰልፉን በጋራ መጥራት ለምን […]

በአፍሪቃ እስካሁን 3000 ቤቶች ሌት ብርኃን እንዲያገኙ አስችሏል። ኤሌክትሪክ ፈፅሞ ባልነበረበት ቦታ የኤሌክትሪክ ኃይል ይዘን እንመጣለን ይላል። ሞቢሶል የተሰኘው ከፀሀይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መሣሪያ የሚፈበርከው ድርጅት።

«ህግን አክብረን ለድርድር የማናቀርበውን ህገመንግስታዊ መብታችንን አሳልፈን አንሰጥም። ታላቁ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 26፣2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይደረጋል፡፡» ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጹ። ፓርቲዉ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አስፈላጊዉን እውቅና ያገኘ ሲሆን ፣ ከትንሳኤ በዓል በኋላ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎችና በአዲስ አበባ […]

ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ጠዋት ላይ ያልታወቁ ታጣቂዎች፣ በቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልል 28 ሰዎች አሣፍሮ ይጓዝ በነበረ ከፍተኛ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ ከፍተው 9 ተሣፋሪዎችን ሲገድሉ በሰባቱ ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የማቁሰል አደጋ አድርሰዋል።

ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት እያጠና መሆኑን ገልጿል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ – ኦፌኮ ባለፈው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ በጠራው ህዝባዊ ስብስባ ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለማስተሳሰር በወጣው ማስተር ፕላን ላይ ተቃውሞውን ገልጿል፡፡

ኦፌኮ ይህንን ያሳወቀው ያካሄደውን ምክክር ተከትሎ ባወጣው የአቋም መግለጫ የከተሞቹን ነዋሪዎች የሚጎዳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ መሆኑ ታውቋል፡፡

“የኦሮሞ ገበሬዎች  እየተነቀሉ ቦታቸው በሊዝ የሚሰጠው ለመሬት ቅርምት እንጂ ለልማት አይደለም” በማለት ኦፌኮ ተቃውሞውን አሰምቷል።

ዋና ፀሐፊው አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ የሰጡትን መግለጫ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

የደቡብ ሱዳን ፀረ-መንግሥት ኃይሎች የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማይቱን ቤንቲዩን መቆጣጠራቸውን የመንግሥቱ ኃይል የሆነው የሱዳን ሕዝብ አርነት ሠራዊት – ኤስፒኤልኤ ዛሬ አረጋግጧል፡፡

መንግሥቱ አክሎም ተቃዋሚዎቹ ምናልባት ድጋፍ ከኻርቱም አግኝተው ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም መልዕክት ቢያስተላልፉም አማፂያኑ ግን ይህንን የጁባን ውንጀላ ፈጥነው ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ቤንቲዩ ላይ ሁለቱም ወገኖች ገና እየተፋለሙ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያደምጡ፡፡

 

ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ህፃናትን ሞት ቁጥር በሁለት ሦስተኛ መቀነስ ብትችልም በሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የሠፈረው ግብ ላይ እንዳልደረሰች ተገለፀ።

የእናቶችን ሞት ለመቀነስ አሁንም ብዙ እንደሚቀር ተገልጧል።
የአውሮፓ ኅብረት እነዚህን ግቦች ለመምታት ያግዝ ዘንድ አርባ ሚሊዮን ዶላር ለግሷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካችው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ ልኮልናል።

(2007-2008 ዓ.ም)
የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች

ሥር የሰደደ ድኅነትና ረሃብን ማጥፋት፤
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ፤
የፆታዎች እኩል መሆንን ማስተማር እና የሴቶችን ውሣኔ ሰጭነት ማስፋት፤
የሕፃናት ሞትን መቀነስ፤
የእናቶች ጤናን ማሻሻል፤
ኤችአይቪ/ኤድስን፣ ወባንና ሌሎችም በሽታዎችን…

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ሳምንት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነዉ። የዘርፉ ባለሙያዎች ከተማዋ የትራፊክ አደጋ እንደሚበዛባት፤ አደጋዉም በሶስት ዓበይት ምክንያቶች እንደሚከሰት ያስረዳሉ።

ምሥራቅ ዩክሬን ውስጥ መፍቅሬ ሩስያ ሚሊሽያዎች ዛሬ ስድስት ብረት ለበስ ወታደራዊ መኪናዎችን መያዛቸውን ዩክሬን አስታወቀች ። የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር መኪናዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ መጀመሪያ በአካባቢው ነዋሪዎች ከታገዱ በኋላ አክራሪ ኃይሎች እንደወሰዱዋቸው ዛሬ ተናግሯል።

የዓለም ባንክ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት ለመርዳት የሚያስችለው አዲስ የልማት መርሀግብር አወጣ። ባንኩ በዓለም ድህነት አንፃር የጀመረውን ዘመቻ ለማሳካት ከሚመለከታቸው ሀገራት ጋ ፣ ከኢትዮጵያ ጋ ጭምር ተባብሮ ይሰራል።

ነገረ ኢትዮጵያ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡
በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ PDF ያንብቧት

– ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
– የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
– በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
– ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
– እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ –
– ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
– ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
– የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡

በግርማ አንድሪያስ  (ኔዘርላንድ፡ ኣምስተርዳም)

”….ጋዜጠኞችና ኣስታሚዎች በጥብቅ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የጀመሩት የፕሬስ ኣዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ  ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 1984 በአትዮጵያ ኣቆጣጠር። ታስረው በፕሬስ ህጉ የተከሰሱና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክረው ነጻ የወጡት፣ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው የአዲስ ዘመን ጋዘጣ ኣዘጋጆች ናቸው። ኣዘጋጆቹ የታሰሩትና የተከሰሱት በጋዜጣው ላይ በ ኢትዮጵያ የዲሞክራሲን ጎጂና ጠቃሚ ገጽታዎች የሚዳስስ  ጽሑፍ በማውጣታቸው ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ። የሰልፉ ቀን ወይንም ቦታ እንዲቀየር የመጠየቅ እንጂ በጥቅሉ ለቀረቡት የሰልፍ ጥያቄዎች እውቅና አንሰጥም የማለት መብት አስተዳደሩ እንደሌለው በመጥቀስ፣ በአስተዳደሩ የተላከዉን […]


(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ – መጋቢት/፳፻፪ ዓ.ም):- ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት ፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው – ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ:: ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው ። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው::
ሰኞ —- መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። ይህ ቀን አንጽሖተ ቤተመቅደስ የፈጸመበት ሰኞም ይባላል ።ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።
ማክሰኞ —- የጥያቄ ቀን ፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ ?”ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪ ።
ረቡዕ —- ምክረ አይሁድ ፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል ።ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ።ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩–፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል።ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮–፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። ይህች ሴት ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።
ሐሙስ —- ጸሎተ ሐሙስ ፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫–፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮–፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድህነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። 
ዓርብ —- የስቅለት ዓርብ፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው ፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
ቅዳሜ —- ቀዳም ስዑር ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ታባላለች ። ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል ።ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ያባላል።
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

የፌደራሉ አቃቢ ሕግ ከሁለት ወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን አይሮፕላን ወደ ጄኔቭ ከተማ በወሰደው ረዳት አብራራ ኃይለመድኅን አበራ ላይ ክሥ መሠረተ፡፡

አቃቢ ሕግ ኃይለመድኅንን የከሰሰው በማገት ወንጀል ነው፡፡

በመቶ ሺሆች ዩሮ የሚገመት ጉዳት መድረሱም በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

 

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮች በመንግሥቱ የተሣሣቱ ፖሊሲዎች ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ክሥ አሰማ፡፡

ለችግሮቹም በአስቸኳይ መፍትኄ እንዲሰጥ፣ ካለበለዚያ ሥልጣኑን እንዲለቅቅ የሚጠይቅ ሰልፍ እጠራለሁም ብሏል፡፡

መንግሥት በበኩሉ “አሉ” ስለሚባሉት ችግሮች የሚቀርቡት ክሦች የተጋነኑ ናቸው ይላል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ኃይሎች ነዳጅ ዘይት አምራቿን የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማ ቤንቲዩን መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጊያው ከተማይቱ ውስጥና በአካባቢዋ እንደቀጠለ መሆኑን የሃገሪቱ የጦር ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

አንድ ማንነቱን መግለፅ ያልፈለገ የቤንቲዩ ነዋሪ የተፈጠረውን ሁኔታ ለቪኦኤ በስልክ አረጋግጧል፡፡

የተቃዋሚዎቹ መሪዎች የነዳጅ ዘይት ምርቱን የማቋረጥ ሃሣብ እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ግጭት ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ። የርስ በርስ ግጭቱን ለማስቆም እዚያ የሚገኘውን የፈረንሳይና የአፍሪቃ ህብረት ኃይል ለማገዝ የአውሮፓ ህብረት ወታደሮችን ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ። በዚሁ ዘመቻ ጀርመን ተካፋይ ብትሆንም ተሳትፎዋ መገደቡ ግን አስተችቷታል።

የአዉሮጳ ኅብረት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ። በሉክዘምበርግ ትናንት የተሰባሰቡት የኅብረቱ የ28 ሃገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንብረት የማንቀሳቀስና የቪዛ እገዳ ለማሳረፍ በሙሉ ድምፅ መስማማታቸዉ ተገልጿል።