በሰሜን ጎንደር የመንግስት ሹመኞች የለኮሱት ግጭት ደም አፋሳሽ ሆነ ቀጥሎአል
ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሆን ብለው በቀሰቀሱት ግጭት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እየተፈናቀሉ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት ጥቃቱን የሚፈጽሙት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው የመንግስት ሚሊሺያዎችና አስተዳዳሪዎች ናቸው። አንድ ባሏ ፊቷ ላይ የተገደለባት ሴት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በመንግስት አቀናባሪነት መፈጸሙን ገልጻለች። ታጣቂዎቹ …