በኦሮሚያ ክልል ውጥረቱ አይሏል::ተቃውሞ ዳግም እንዳይፈነዳ ያሰጋል::በድሬዳዋ ካምፓስ ተቃውሞ እየተደረገ ይገኛል ። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎EPRDF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ተቃውሞ ቀዝቅዟል በሚል ኦሕዴዶችን ግምገባ አስገብቶ እየጠበጠበ በማባረር ላይ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ ቃገዛዝ በኦሮሚያ ክልል ያለው ተቃውሞ ዳግም ያገረሻል …

በኦሮሚያ ክልል ውጥረቱ አይሏል::ተቃውሞ ዳግም እንዳይፈነዳ ያሰጋል::በድሬዳዋ ካምፓስ ተቃውሞ እየተደረገ ይገኛል ። Read more »

የኢሕአዴግ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ግዙፉ ቅጽር ግቢ ውስጥ የሚገኘው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ላይ ዘረፋ መካሄዱ ተሰማ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን ዝርፊያ፣ የካቲት 19 ወይም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ሳይከናወን እንዳልቀረ ተገልጿል፡፡ …

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ላይ ዘረፋ መካሄዱ ተሰማ፡፡ Read more »

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የንግድ ከተማ በሆነችው ዱባይ ውስጥ፣ ሰባት ኢትዮጵያውያን ሥጋ ላኪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ፡፡ ሥጋ ላኪዎቹ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እንዳይወጡ የተደረጉት፣ ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በዱባይ በተደረገው ‹‹ገልፍ ፉድ›› ኤግዚቢሽን ላይ ከተሳተፉ …

ዱባይ ውስጥ ሰባት ኢትዮጵያውያን ሥጋ ላኪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ የተሰወሩም አሉ:: Read more »

የኦሕዴድ የብኣዴን አመራሮችና አባላት በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መሪነት ግምገማ ተቀምጠው እየተናከሱ ይገኛሉ:: የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ኦነግ እና ለውጥ ፈላጊው ሃይል የኦሕዴድን መዋቅር ተጠቅሞ በኢሕኣዴግ ላይ ሕዝቡን አሳምጿል ድርጅታችንን ገበናውን አጋልጣችሁ ሰጣችኋል ወዘተ በሚሉ አጠቃላይ ወቅታዊ የኦሮሚያ ጉዳይ ዙሪያ የኦሕዴድ …

የኦሕዴድ የብኣዴን አመራሮችና አባላት በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መሪነት ግምገማ ተቀምጠው እየተናከሱ ይገኛሉ:: Read more »

“በሀገሪቱ የተፈጠሩ ግጭቶች፤ የዲሞክራሲና መብት እጦት መገለጫዎች ናቸው” – ቃዋሚዎች “የሀገር ሽማግሌዎች በጉዳዩ ጣልቃ መግባት አለባቸው” የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ – ወ/ጊዮርጊስ ዘንድሮ ኦሮሚያን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ተቃውሞዎችና ግጭቶች ዋነኛ መነሻቸው የዲሞክራሲና የመብት ጥያቄዎች መሆናቸውን አንጋፋ ፖለቲከኞችና ተቃዋሚዎች ገለፁ፡፡ …

“በሀገሪቱ የተፈጠሩ ግጭቶች የሀገር ሽማግሌዎች በጉዳዩ ጣልቃ መግባት አለባቸው” የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ – ወ/ጊዮርጊስ Read more »

• 11 ዋና አከፋፋዮች ታስረዋል፤ የዋስትና ጥያቄያቸው በፍ/ቤት ተቀባይነት አላገኘም • በርካታ ሺ ሰዎች በአባልነት ተመዝግበዋል መግቢያ 4ሺ ብር ይከፈላል • ቲያንስ 700 ገፅ ደብዳቤ፣ የ15ሺህ ሰዎች የድጋፍ ፊርማ ለጠ/ሚ ቢሮ አስገብቻለሁ ብሏል የቻይናው ኩባንያ ቲያንስ፤ ሰፊ የምልመላ ዘመቻ በርካታ …

የ“ቲያንስ” ኔትዎርክ መሪዎች እየታሰሩ ነው Read more »

·        ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው(አባ ማቲያስ ሕዳር 2008)

·        ከቫቲካን ጋር የነበረንን የቀድሞ ፍቅር(?) እንመልሰዋለን(አባ ማቲያስ የካቲት 2008)

·         ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስትያንን የገዛ ቅኝ ገዥ ነው(አባ ማቲያስ ጥቅምት 2008)
·        ወራሪዋን ቫቲካንን ፍቅር : ልጆቻቸውን ቅኝ ገዥ— አባት ብሎ ዝም!!

(ዘአዲስ እንደፃፉት):- አባ ማቲያስ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ትግራይ ሄደው ጉብኝት ማድርጋቸው ይታወሳል:: አዲግራት ላይ የአዲግራቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቦታ ላይከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነውበማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል:: http://www.addisadmassnews.com/images/Issue-826.pdf

ሀገራዊ ማህበራዊና ብሔራዊ በሆነ ጉዳይ ላይአንተ ኦርቶዶክስ : አንተ ካቶሊክመባባሉ ሳይኖር የሁሉም እምነት ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአንድነት መቆም እንዳለበት ግልጽ ነው:: “ኦርቶዶክስና ካቶሊክ መካከል ያለው ልዩነት ጠባብ ነውብሎ የማይመስል ነገር መናገሩ ( ያውም ከፓትርያርኩ አንደበት) ግን እጅግ የሚያስተዛዝብና ግምት ውስጥ የሚጥል ስህተት ነው:: የሆነው ሆኖ ይህን ባሉ በሶስተኛው ወር የካቶሊኳ ራስ ቫቲካን ደርሰው የበርካታ ኢትዮጵያውያንን አንጀት አቁስለው ተመልሰዋል::

 ፓትርያርኩ ቫቲካን መሄድ ነበረባቸውን?

በመሰረቱ: ቫቲካን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እጅግ የመረረ ግፍ ፈጽማለች:: ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር : የቫቲካን ጳጳሳት የመርዝ ጋዝ እየባረኩ ኢትዮጵያን ለመውረር የሚደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት እንደሆነ አውጀዋል:: የወርቅ መስቀላቸውን ሳይቀር ለጦርነቱ አዋጥተዋል:: የሙሶሎኒምና የግራዚያኒ ቀኝ እጅ የነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ ባደባባይ ወረራውን ደግፎ መግለጫ ሰጥቷል::

(http://www.globalallianceforethiopia.org/italianinvasion.pdf)

ፋሺስት ጣልያን አንድ በዛ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ገድላለች:: በሺዎች የሚቆጠሩ ካህናትን አቃጥላለች:: በውል የታወቁትን እንኳን ብንቆጥር ወደ 2 ቪህ አብያተ ክርስቲናትን አውድማለች:: ጣልያን ከመውረሯ በፊትም የጣልያን ሰላይ እየሆኑ ይሰሩ የነበሩት የቫቲካን መነኮሳት ነበሩ::

ቫቲካን ስለሰራችው ጥፋት ኢትዮጵያንን እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ስላልሆነች : ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የቫቲካንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ቫቲካን ይቅርታ እስካልጠየቀች ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባቶች ከቫቲካን ጋር አንድነት እንዳይኖር በመወሰናቸው የሁለቱ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ( የአለቃ አያሌውመች ተለመደና ከተኩላ ዝምድናመጽሓፍን ይመልከቱ)

በተለይ አሁን በቅርቡ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ ጣልያን ውስጥ ሀውልት እንዲቆም ከተወሰነ በኋላና የቫቲካን ጳጳሳትም ይህን ጉዳይ የመደገፋቸው ዜና በመሰማቱ : በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በማሰማታቸው የሃውልቱ ስራ ቆሟል:: እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቫቲካን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ ቢወተውቱም : ቫቲካን ካላት ንቀት የተነሳ ፈቃደኛ አልሆነችም:: የሙገርመው ግን ጀርመን ናዚዎች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ዝም በማለቴ ( ባልሳተፍበትም) ይቅርታ ጠይቃለሁብላ አይሁዶችን ይቅርታ ጠይቃለች::

(https://www.gopetition.com/…/vatican-apology-for-ethiopian-…)

ራሷ የጨፈጨፈችውንና ያስጨፈጨፈችውን ኢትዮጵያውያንን ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ : ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እስክትጠይቅ ድረስ ይፋዊ ግንኙነት እንዳይኖር በኢትዮጵያ በኩል ተወስኖ ነበር:: የአለቃ አያለውውን መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና ያነቧል::

አባ ማቲያስ ግን ያንን እግድ ጥሰው ቫቲካን ድረስ በመሄድእኛና ቫቲካን ድሮም ፍቅር ነን: የድሮውን ፍቅር እንመልሰዋለንበማለት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ድካም መና አብልተውታል::

የአባ ማቲያስ ቫቲካን መሄድ እንግዳ ቢሆንም ብዙዎእዛው ሀገራቸው ላይ ሄደው ቫቲካን ለሰራችው በደል ይቅርታ ትጠይቅብለው ይናገራሉ ተብሎ ተጠብቆም ነበር:: በተገላቢጦሹ ግን አባ ማቲያስድሮም እኛና ቫቲካን ፍቅር ነበርን ወደፊትም ያንን ፍቅር እንመልሰዋለንብለው አረፉት::

የቀደመው የቫቲካንና የኦርቶዶክስ ፍቅር የቱ እንደሆነ አልገባኝም:: የዲዮስቆሮስ ይሆንን? ከጥንት ጀምሮ ቫቲካን የምትልካቸው ሚሺነሪዎች ሕዝብ ሲያጨፋጭፉ ነገር ሲተክሉ እንጂ ፍቅር መስርተው ሲሄዱ አይታወቅም:: እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን መጥቀስ ይቻላል:: ቃል በቃልኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ ሁለት እሾክ ተክዬባት ሄድኩእስከማለት የደረሱ ናቸው:: ጸጋና ቅባትን ያስትውሷል:: ጂሴፔ ሳፔቶና አባ ማስያስም ኢትዮጵያን ለጋ ቅቤ ሲቀቡ አናቃቸውም:: በሁለቱም የጣልያን ጦርነት ወቅትም ቫቲካን የሰራችው ወንጀል እንጂ የፍቅር ስራ አይደለም:: (አቡነ ጎርጎርዮስ ////ታሪክ)

የኦርቶዶክስና የቫቲካን የቀደመ ፍቅር የቱ እንደሆን አይገባኝም:: ፓትርያርኩ እንደዛ ከሚሉቫቲካን አትፍታለችና ይቅርታ ትጠይቅ,ኢለውን ያባቶቻቸውን ቃል አጽንተው እሳቸውም ይሄን ቢያደርጉ ለነፍሳቸውም ለስጋቸውም ታሪክ ነበር:; ማኅበረ ቅዱሳንንቅኝ ገዥያለ አንደበት እውነተኛዋ ቅኝ ገዥን ምን ይላት ይሆን ብዬ ጠብቄም ነበር::

ምን ያደጋል ! አባታችን አገላበጡት

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

• ከለጋሾች ገንዘብ ካልተገኘ፣ በግንቦት ወር የእርዳታ እህል ይሟጠጣል” ተመድ • እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው የዓለም ሀገሮች፣ ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች በኢትዮጵያ ድርቅ ያስከተለው ከባድ የረሃብ አደጋ፣ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ለአገሪቱ ፀጥታ ጠንቅ እንዳይሆን የአሜሪካ መንግስት እንደሰጋ የዘገበው ሲኤንኤን፣ ሃያ የረድኤት …

በኢትዮጵያ የረሃብ አደጋ፣ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ለአገሪቱ ፀጥታ ጠንቅ እንዳይሆን የአሜሪካ መንግስት ሰጋ Read more »

ፍለጋ እጅግአየሁ ወዴት ነሽ; እንዲህ እንደዛሬ የባለእዳነት ስሜት ሲጠጋኝ፣ እንዲህ እንደዛሬ ላገኘኋቸው ደስታዎች በመልሱ ያልከፈልኩት ብድር እንዳለ ሳስብ እልፍ ጥያቄዎች ይጎበኙኛል፡፡ ነፍስ ድረስ የሚደርስ፣ የጠለቀ እና በየጊዜው የሚታደስ እንዲሁምየሚጎመራ ደስታ ከማገኝባቸው የኪነጥበብ ስራዎች መሀል ደግሞ የእጅግአየሁ ሽባባው ዘፈኖች በቀዳሚው ተርታ …

ፍለጋ እጅግአየሁ ወዴት ነሽ; Reyot TV – ቴዎድሮስ ጸጋዬ Read more »

መገናኛ ብዙሃንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም። ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም። አስር …

የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች – ክንፉ አሰፋ Read more »

የ20 ዓመት ወጣትና የዐሥረኛ ክፍል ተማሪ ሞቱማ ፈዬራ በታጣቂዎች መገደሉን ለቤተሰቡ ቅርበት እንዳላቸው የገለጹ ምንጮች ሲናገሩ፤የወረዳው መስተዳድር በበኩላቸው የሟቹን አስክሬን መመለከታቸን ተናገረው ‘በማን ተገደለ?’ ስለሚለው ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገለፀዋል፡፡ ዋሽንግተን ዲሲ — ባለፈው ሣምንት ረቡዕ የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም …

በሚያጠናበት ቤት ስለተገደለው ተማሪ ሞቱማ ፈዬራ አሟሟት (VOA) Read more »

‹ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ እየኖርኩ ነው›› አትሌት መቶ አለቃ ታደሠ ሰጥ አርጋቸው #Ethiopia #ቁምነገርመጽሄት አትሌት መቶ አለቃ ታደሠ ሰጥ አርጋቸው እድሜያቸው ገፍቷል፡፡ 78ኛ አመታቸውን ይዘዋል፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ከወርቅ እስከ ነሐስ ሜዳልያዎች …

‹ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ እየኖርኩ ነው›› አትሌት መቶ አለቃ ታደሠ ሰጥ አርጋቸው Read more »

የአርባ ምንጭ –ጂንካ መንገድ ተዘጋ ዛሬ የካቲት 25/08 በኮንሶ ከተማ የመከላከያ ኃይል ከህዝቡ ጋር በፈጠረው ግጭት የኮንሶ ልዩ ወረዳ ዋና ከተማ ካራት ውስጥ የጥይት ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡ ወደከተማዋ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሰረት ግጭቱ የተነሳው እስከ ፌዴሬሽን ም/ቤት የደረሰውን የአካባቢው ህዝብ …

የአርባ ምንጭ –ጂንካ መንገድ ተዘጋ Read more »

አለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ምነው ይህን ቱባ ዜና ዝም አሉ::ሕዝብ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰላችቷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎TPLFHoax‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ የገባበትን አጣብቂኝ እና የሕዝብ ተቃውሞ መወጣት ሲያቅተው አቅጣጫ ማስቀየሪያ ዘገባ በፈጠራ ኤርትራን ደበደብኩ ሲል የለመደውን …

አለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ምነው ይህን ቱባ ዜና ዝም አሉ::ሕዝብ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰላችቷል:: Read more »

BBN መረጃ የካቲት 25/2008 ጁሙዓ √=በዛሬው እለት በበኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ መደረጉ ታወቀ √= የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ዛሬ በአንዋር አስገራሚ ንግግር አደረገ የሙስሊሞችን የእምነት ነፃነት መብት በሃይል እና በአፈ ሙዝ ረግጦ እየቀማ ያለው ኢሓዴግ መራሹ መንግስት በዛሬው …

በዛሬው እለት በበኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ መደረጉ ታወቀ Read more »

መብሰል መከባበር መደማመጥ የምንጀምረው ከየትኛው ጫፍ ይሆን? የምንሄድበት መንገድ ሁሉ ዝግ ነው!! የስድብ እና የፍረጃ ፖለቲካ ይሰለቻል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎FreedomofExpression‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎SocialFreedom‬ ‪#‎Tolerance‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የማህበራዊ ድረገጽን ለመልካም ነገር ማዋል ከቆመ ቢያንስ 2 አመታት ተቆጥረውታል:: ማህበራዊ ድረገጽ በተለይ(ይብልጡኑ ፌስ …

መብሰል መከባበር መደማመጥ የምንጀምረው ከየትኛው ጫፍ ይሆን? የስድብ እና የፍረጃ ፖለቲካ ይሰለቻል:: Read more »

ወያኔ የኦሮሞ ጠላት ነው

አንተነህ መርዕድ

Abayi Tsehaye አባይ ፀሐዬ

መለስ ሲያጉረመርምበት ብርክ የሚይዘውና የሚሙለጨለጨው፣ ጓደኞቹን ደጋግሞ በፍርሃቱ የሸጠው አባይ ፀሃዬ ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ከሱ የተሻሉና የሚያስፈሩት ህወሃቶች የሌሉ መሆናቸውን በማረጋገጡ በየመድረኩ ብቅ እያለ መፎከርና መዘባረቅ የእለት ተእለት ሥራው ሆኗል። በተለይም በዋና ባለቤትነት የአዲስ አበባን መሬት ሸጦ ከጨረሰ በኋላ የአካባቢውን ገበሬዎች ከነመሬታቸው ሊቀራመት ያደባበት ተንኮል አልሠራ ሲል “ልክ እናስገባቸዋለን” ሲል ፎከረ። አሁን ደግሞ ፉከራው የለኮሰውን እሳት ማዳፈን ተስኖት “ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አይደለም” የሚል የሽሽት ሽምጥ ሩጫ ይዟል። እሳቱ ግን እሱን ሳይለበልበው የሚመለስ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

በግምት ከሃያ አራት ዓመታት በፊት ይሆናል ቀኑ። በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም እንዲኖር ብዙ ጊዜ የሚደክሙና የሚጸልዩ፣ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሚባሉ አንድ መንፈሳዊ አባት፣ ምዕመናንን ሲያስተምሩ የተናገሩት፣ ሁልጊዜ የማስታወሰውና የማልረሳው አባባል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጌታቸው ኃይሌ

Identity crisis ማነኝ?

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ማንነት ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖ ቈይቷል። የሥነ ልቡና ምሁራን identity crisis የሚሉት ነው እንዳልል ያተኰረው “እኔ ማነኝ” ከሚለው ላይ አይደለም። ያተኮረው “ማንነት ከመሬት ጋር ይያያዛል ወይስ አይያያዝም?” ከሚለው ጥያቄ ላይ ነው። ውይይቱን እንዳዳመጥኩትና እንደሰማሁት፣ እኔም አስተያየቴን እንድሰጥ ተጠይቄ እንደተቸሁት፣ ማንነትን ከመሬት ጋር የሚያያይዙ እምነታቸውን ከኃይማኖት እምነት ደረጃ አድርሰውታል። ስለዚህ እነሱን በማስረጃ ማሳመን ሃይማኖታችሁን ለውጡ እንደማለት ሆኗል። “እምነቱ ሀገር አጥፊ ነው፤ ተውት” ቢባሉም፣ ማንነታቸው ከያዙት መሬት ጋር ከተቆራኘ፣ ይህ አደገኛ አቋማቸው ለሚያስከትለው ሀገራዊ ችግር አንዳች ሥጋት አይታይባቸውም። ክልል ይዞ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል የሚሉም አይጠፉም። መሳሳታቸውን መስማት አይፈልጉም፤ ግን ማንነት የሚዘራበት መሬት የሚያስፈልገው ዳጉሳ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

የአበው ተረት ለልጅ የሳቁለት ለውሻ የሮጡለት ነው የሚለው። ለፖለቲከኛ ያጨበጨቡለት የሚል ቢጨመርበት ተስማሚ ይመስለኛል። ልጅ ከሳቁለት ሁሉ ቦታ እየገባ ነገር ያበላሻል፤ ውሻ ከሮጡለት ጥሎ ካላንደባለለ ወይ ካልቦጨቀ አይመለስም ፖለቲከኛም ካጨበጨቡለት አበው ልቤ አደገና ያለ ቁመቴ አላስገባ አለኝ የገዛ ቤቴ እንደሚሉት ይሆንና ከእኔ በላይ ለአሳር በሚል መታበይ ብዙ ጥፋት ያደርሳል ኋላም ራሱን ያዋርዳል። እኛም ጥሎብን ይሁን ባህል ሆኖብን ባይታወቅም እየኮተኮቱ ማሰደግ እየገሩ ለወግ ማዕረግ ከማብቃት ይልቅ እያሞካሹ ማበላሹትን እያጨበጨቡ ወደ ገድል መግፋቱን ተክነንበታል። በዚህ መንገድ ስንት ለሀገርና ለወገን ሊጠቅሙ ይችሉ የነበሩ ሰዎችን አጥተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኦሮሚያ ክልል ጭር ብላለች::መንገዶች እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ተዘግተዋል::ተቃውሞው ቀጥሏል::‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EthiopiaDriversstrike‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎AddisAbaba‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ራሱ በሰራው ወንጀል ሕወሓት ሕዝብ አይነካ ብለዋል የተባሉትን የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ካባረረ በኋላም የሕዝብ ተቃውሞ መብረድ አልቻለም::በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተሰበሰበው …

የኦሮሚያ ክልል ጭር ብላለች::መንገዶች እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ተዘግተዋል::ተቃውሞው ቀጥሏል:: Read more »

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በጎንደር ስብሰባ ተቀመጡ:: የሕወሓት የ30 አመት ወንጀሎች ተተንትነዋል:: Minilik Salsawi በሕወሓት የተዘረፈባቸውን ማንነት እና መሬት ለማስመለስ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በጎንደር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል:: በጎንደር ከተማ ላንድ ማርክ ሆቴል ዛሬ የተካህደው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች ስብሰባ ቁጭት እና እልሕ …

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በጎንደር ስብሰባ ተቀመጡ::የሕወሓት የ30 አመት ወንጀሎች ተተንትነዋል:: Minilik Salsawi Read more »

በደሴ እና በአቅራቢያ ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Dessie‬ ‪#‎TaxiDriversStrike‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Change‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከወሎ ክፍለሃገር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በደሴ እና አከባቢው ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::የወያኔ ፖሊሶች እና ካድሬዎች ታርጋ …

በደሴ እና በአቅራቢያ ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል:: Read more »

ሰሞኑን ተግባራዊ የሆነውን የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 208/2003ን በመቃወም አድማ አድርገው የነበሩት የታክሲዎች ማኅበራት፣ ባሏቸው ጥያቄዎች ላይ ድርድር አድርገዋል፡፡ የታክሲ አሽከርካሪዎች በተለያዩ እርከኖች የተቀመጡትን ጥፋቶች ለሁለተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ጥፋት ሲፈጸም 14 ነጥቦች ያህል ከሞላ፣ ለስድስት ወር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ …

የአዲስ አበባ የታክሲ ማኅበራት በድርድር ወደ ሥራ ተመልሰዋል Read more »

በኦሮሚያ የፀጥታ መደፍረስ ሳቢያ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ አቶ በከር ሻሌ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ፖሊት ቢሮ፣ ከወራት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል ከተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ሁለት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ወሰነ፡፡ …

የኦሕዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌና የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኩቹ ከሥልጣን እንዲነሱ ተደረጉ፡፡ Read more »

በወልቃይት ጠገዴ ውጥረቱ የተባባሰ ሲሆን ሕወሓት 70ሺህ የትግራይ አባወራዎች ሰፈራ ሊተገብር ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎Welkaite‬ ‪#‎Tigray‬ ‪#‎Amhara‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ቀብር/ለቅሶ እንሂድ ሲሉት ሰው ነው ትግሬ የሞተው የሚለው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማልፈልገው እና ያልሆንኩት የትግራይ ማንነት …

በወልቃይት ጠገዴ ውጥረቱ የተባባሰ ሲሆን ሕወሓት 70ሺህ የትግራይ አባወራዎች ሰፈራ ሊተገብር ነው:: Read more »

አድዋ እና አባጅፋር ”አባጂፋር ለኢትዮጵያ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል። ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር ሀዲድ ሲዘረጋ አባጂፋር ገንዘብና የሰው ኃይል ልከዋል። ለሀዲድ ዝርጋታ እና ድልድይ ሥራ በ1892፣ 1894 እና 1900 አባጂፋር የሰው ኃይል ወደ አዲስ አበባ ልከዋል። የባቡር ሀዲዱንና ከባባድ አስፈላጊ …

አድዋ እና አባጅፋር (3ቱ አፄዎች እና ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አህመዲን ጀበል) Read more »

አዲስ አበባ ቃሊቲን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ስራ እንዳቆሙ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EthiopiaDriverStrike‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ የወያኔ መንግስት ያወጣን የአሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪዎች ሕግ በመቃውም የአዲስ አበባ ታክሲ ሹፌሮች ማህበር የጠራውን የሁለት ቀን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የሾፌሮች አድማ …

አዲስ አበባ ቃሊቲን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ስራ እንዳቆሙ ነው:: Read more »

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Adwa120‬ ‪#‎Oromoprotests‬ : ሁላችንም ታስረናል !!! የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አና ኣባላት በ፻፳(120)ኛው የኣድዋ ድል በዓል ላይ በምንሊክ አደባባይ አጋርነታቸውን በኣምባገነን ለሚሰቃየው ሕዝብ ኣሰምተዋል። ‪#‎MinilikSalsawi‬ –እንዲሁም የኣዲስ ኣበባ ወጣቶች የዳግማዊ ምንልክን ምስል በመያዝ አና ምስላቸው ያለበትን ካኒተራ በመልበስ ለኣድዋ ድል …

ሁላችንም ታስረናል !!! በ120ኛው የኣድዋ ድል በዓል ላይ በምንሊክ አደባባይ Read more »

  ዓድዋ ሲታሰብ – ተጻፈ በ  ሔኖክ ያሬድ ምስል መግለጫ፡-  – ከላይ የዓድዋው የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በሠዓሊው ምናብ – ከመሃል በግራ ዳግማዊ ምኒልክ የኢጣሊያውን መሪ ክሪስፒን ሲጎሽሙትና ሲጥሉት በ‹‹ለ ፐቲት ጆርናል›› የታተመ የካርቱን ሥዕል፣ አዝማሪ ፃዲቄ እየሸለለችና እየፎከረች ስታዋጋ በሠዓሊው …

ዓድዋ ሲታሰብ Read more »

(ማርች 2/2016/ የካቲት 23/2008 ዓ.ም):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወደ ቫቲካን ጉዞ ማድረጋቸው እና ከሮማማው ፓፓ “ፖፕ ፍራንሲስ” ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል፡፡ ሲጨባበጡ፣ ትከሻ ለትከሻ ተሳስመው ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ ፓትርያርካችን ለፖፕ ፍራንሲስ ማስታወሻ መስቀል እና መጽሐፍ ሲሰጡ ሁሉ አይተናል።
የሁለቱ መሪዎች ዋነኛ የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የክርስቲያኖች መከራ፣ ስደትና የቤተ ክርስቲያን ውድመት እንደሆነ ከፖፑ ንግግር መረዳት ይቻላል። “የክርስቲያኖች የሰማዕትነት ደም የክርስትና ዘር ነው” የሚለውን ታዋቂ ቃል አንስተው ፖፑ ማብራራታቸው ተዘግቧል። ዝርዝሩን መመልከት ለሚሻ ዜናው ወደተዘገበባቸው ሥፍራዎች ጎራ ማለት ይችላል።

ሁለቱም መሪዎች ከተሾሙ ብዙም አልቆዩም። ፓትርያርክ ማትያስ February 28/ 2013፤; ፖፕ ፍራንሲስ ደግሞ    በቀናት ልዩነት March 13/ 2013 ነው የተሾሙት። ሁለቱም መሪዎች በአማኞቻቸው የሚታዩበትን ጠባይ በአጭር ጊዜ ለመቅረጽ የቻሉ ሆነዋል። ያሳዩት ጠባይ ግን ልክ እንደ ልብሳቸው እጅግ የተቃረነና የተለያየ ነው። ፓፓ ፍራንሲስ ልጆችን በማባለግ እና በሌሎችም አስነዋሪ ተግባራት ስሟ የጎደፈውን የካቶሊክን ቤተ ክርስቲያን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስሟን ለማደስና በዓለም ሕዝብ ዘንድ ያላትን ተቀባይነት እጅግ በላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ችለዋል።
ፓፓው ከሠሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለረዥም ዘመናት ተለያይተው የነበሩትን ኩባንና አሜሪካንን ለማስታረቅ ድልድዩን ያበጁትና ታሪክ የሠሩት እርሳቸው መሆናቸው ነው። ኮሚኒስቱን የኩባ አስተዳደር ከደመኛ “ኢምፔሪያሊስት ጠላቱ” ከአሜሪካን መንግሥት ጋር ለማግባባትና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የፈረሰውን የግማሽ ምዕት የግንኙነት መስመር ለመጠገን ችለዋል።
ከዚህም በላይ ፓፓው በዓለም አማኝም ኢ-አማኒም ሕዝብ ዘንድ ሞገስ ያሰጣቸው ለድሀውና ለዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖረው ለመላው የዓለም ሕዝብ ያሳዩት ጥብቅና፤ ገንዘብ አምላኪውን የዘመናችንን ሉላዊ ሥርዓት በይፋ እየተቃወሙ ለአገሮች ኢኮኖሚያዊ ጤንነት ያሳዩት ወገንተኝነት ነው። ድህነትን እንደበሽታ ለሚጠየፉ ብዙ ቅንጡዎች እና ቅምጥሎች ትልቅ ትምህርት በሚሰጠው ተግባራቸው ከኦባማ ዋይት ሐውስ እና የአሜሪካ ኮንግረስ እስከ ደቡብ አሜሪካ የተለያዩ  አገሮች ግድ የለሽ መንግሥታት ድረስ ምክራቸውን እና ተግሳጻቸውን አሰምተዋል።
የቅምጥል ኑሮን የሕይወታቸው መመሪያ በማድረግ ረገድ ከዓለማውያኑ የባሱት መንፈሳውያን የእምነት መሪዎች በሆኑበት በዚህ ዘመን ፖፕ ፍራንሲስ የቫቲካንን ወደር የለሽ የድሎት መኪናዎች ለመጠቀም አሻፈረኝ በማለት እና እዚህ ግቢ የማትባል የግል መኪናቸውን በመጠቀም በንግግራቸውም በግብራቸው ቅምጥልነትን አውግዘዋል።

ለጉብኝት በሑዱባቸው አገሮች በአጃቢ የተሸለሙ መኪኖቻቸወን በማቆም እና በመንገድ ላይ ከሚጠብቃቸው ሕዝብ ጋር በተለይም ከሕጻናት እና የተለያየ በሽታ ካለባቸው ሰዎች ጋር በመገናኘት፣ እንኳን ለመንካት ለማየት እጅግ የሚፈትን በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሳይጸየፉ በማቀፍና ርኅራኄ በማሳየት ብዙዎችን አስደምመዋል። ሌሎችንም የታዘብናቸውን ብዙ ተግባሮቻቸውን መጥቀስ ይቻላል። ለዚህ ፅሑፍ ሲባል በዚሁ እንግታውና የኛው ፓትርያርክ ሊሟሯቸው ስለሚችሏቸው ነገሮች እናንሣ።

መቸም አንድ የኦርቶዶክስን አባት ከካቶሊክ መሪ “ይህንን ተማር፣ ይህ መልካም የሆነ የኮቶሊኩ መሪ ተግባር ነው” ማለት ችግር ላይ ሊጥል የሚችል ነገር እንደሆነ ይታወቃል። “ካቶሊኮችን ያመሰግናሉ” የሚል የነገረ ሰሪ ጥላሸት ሊያስቀባም ይችላል። በቀድሞው ዘመን ቢሆንማ “ሰዎቹ ኮተሎኩ” ሊያሰኝም ይችል ነበር።
ይሁን እንጂ ቅ/ያሬድ ከዚያች ትል መውደቅንና መነሣትን ተምሮና ተገንዝቦ፣ ሕይወቱን አርቆ ለቤተ ክርስቲያናችን ዓይን እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም በሥላሴ አርአያ ከተፈጠረ ከሌላው ሰው (አማኝም ሆነ የማያምን፤ ኦርቶዶክስም ሆነ ካቶሊክ) መማር መቻሉ ያስመሰግነዋል እንጂ አያስነቅፈውም። ከባዶ ግብዝነትም ያድነዋል።
ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ …. ከላይ እንዳየነው ፓትርያርክ ማትያስ ከፖፕ ፍራንሲስ በቀናት ልዩነት ነው የመሪነት መንበር የተቀበሉት። ነገር ግን በነዚህ 3 ዓመታት ምን ሠሩ ብለን ብንገመግም ከፀብና ከዓምባ ጓሮ፣ በአደባባይና በሚዲያ ከሚሰጡት አሸማቃቂ ንግግር ባለፈ እንዲሁም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት በመራቅ ቤተ ክርስቲያንን ተደራጅተው ከሚዘርፉ ሰዎች ጋር ከመወዳጀት ሌላ መልካም ስም ያተረፉ አይመስለንም።
የካቶሊኩ ፓፓ ለድሆች ጠበቃ መሆናቸውን አይተናል። የኛዎቹም ለኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ጠበቃ ሊሆኑ ይገባቸው ነበር። በኑሮ ውድነት፣ በአስተዳደር ብልሹነት፣ በስግብግበነት መሬቱን እና ቤቱን እየተዘረፈ ትዳሩ ለሚፈርሰው ወገናቸው ጠበቃ ሊሆኑ ይገባ ነበር። ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እርስበእርስ በመሸላለምና የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በገፍ በመዝረፍ በተጠመዱበት በዚህ ጊዜ “ኧረ ተዉ!!!” የሚል የአባት ተግሳጽ ሊያሰሙ ይገባ ነበር።
እንደ ካቶሊኩ ፓፓ አስታራቂ እና የተበተኑትን ሰብሳቢ መሆን ቢያቅታቸው የተሰበሰቡትን ለመበተን መትጋት ግን አይገባቸውም ነበር። በዚህ አንድ ዓመት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው ተግባር ብቻ ለታሪካቸው ትልቅ ጠባሳ እንደሚሆን ሊገነዘቡት በተገባ ነበር።
በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገደሉ ክርስቲያኖች አዝነው ሮም ድረስ እንደሔዱት ሁሉ፣ በአገራቸው ለሚጠፋው ሕዝባቸው፤ በመንግሥት ወታደር ዕለት ከዕለት እየተገደለ በየጥሻው ለሚጣለው ወገናቸው፤ ማዕከላዊን ጨምሮ በየእስር ቤቱ በማሰቃያዎች ለሚንገላታው ወገናቸው ጠበቃ መሆን ይችሉ ነበር።
ድሃ አደጉንና ዕጓለ ማውታውን ለመሰብሰብ ከአበው ሌላ ማን ይመጣል። ቤተ ክህነቱ ከገባበት አስረሽ ምቺው ተላቆና የምንኩስና አሰረ ፍኖቱን ተከትሎ ከዚህ የመንደላቀቅና የመሽቀርቀር አዚም ሊገላገል፣ ለድሃውም ሊያዝን ይገባው ነበር። የካቶሊኩን ፓፓ ካነጋገሩ አይቀር ይህንን ይህንንም ከእርሳቸው ይማሩ። ፓትርያርካችን ሆይ! በእርስዎ ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን ስሟና ታሪኳ ይገነባል ወይስ ይፈርሳል?  
   
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና እየተስፋፋ የመጣውን ‪#‎OromoProtest‬ በማስመልከት የኣውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት በቀጥታ የሰጡት መልስ የተከበሩ ኣቶ Decke, በኢትዮጵያ የኦሮሞን ማህበረሰብ ወቅታዊ ሁኔታ ኣሳሳቢነት በመግለፅ ጥር 14, 2016 የላኩልኝን ደብዳቤ እንዳገኘሁት ላረጋግጥሎት እወዳለሁ። የኣውሮፓ ፓርላማ ይህ ኣሳሳቢ ሁኔታና በኢትዮጵያ ያለው …

ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና እየተስፋፋ የመጣውን ‪#‎OromoProtest‬ በማስመልከት የኣውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት በቀጥታ የሰጡት መልስ Read more »

በፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን፣ መሪ ስቴት ዪኒቨርሲቲ፤ (ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ አንዱዓለም ተፈራ እንደተረጎመው) ትርጉም ከማይሠጠው በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን ለማሰማት በተነሳሱት ላይ የገዥው ፓርቲ ከፈጸማቸው ግድያዎች በተጨማሪ፤ አሁን በቅርብ የወጡት ቁንፅል የቪዲዮ ቅንብሮችና የዜና ዘገባዎች፤ እኒሁ በኦሮሚያ አካባቢ በእምቢታ ቅሬታቸውን ለማሰማት የተነሱት፤ ንብረትና …

ሙስናና በእምቢተኝነት ቅሬታ የሚያሰሙት ንብረት ማቃጠላቸው። ድርጊቱን እናውግዝ ወይስን ይበል እንበል? ተጠያቂው ማነው? – በፕ/ር ሰዒድ ሃሰን Read more »

(http://eotcmk.org):- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ:: ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በምሥራቅ ትግራይ ክለተ አውላሎ አውራጃ አውዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሕይወት ፀዓዱ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ወለተ ክርስቶስ ቢሻው በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዲቁናን ከአቡነ ይስሐቅ፣ ቅስና፣ ቁምስና እና ምንኩስና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተቀብለዋል፡፡

ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የትግራይ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ30 ዓመታት በላይ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ ሳሉ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ዐርፈዋል፡፡
ሥርዓተ ቀብራቸው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ራሳቸው በገደሙትና ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡበት በነበረው ደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ይፈጸማል፡፡
                                                                                                                  
 የአባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አበው ጋር ያድርግልን
አሜን።
         
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

አዋሳኝ ድንበራቸዉም የጦር ሐይል ፍጥጫ፤ ጠብ እና ቁርቁስ ተለይቶት አያዉቅም።አሁን በሰዎች መታገት በተለይ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሐብት እና የሰዉ ሐይል ዋና ዋና ማዕከል ኦሮሚያን በሚንጠዉ ተቃዉሞና አመፅ ሰበብ እንዳዲስ መቀጣጠሉ «የከፋ ይከተላል» የሚል ሥጋት ማጫሩ አልቀረም-እንደ ሮንግ።

የአዲስ አበባ ታክሲዎች አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ አሽከርካሪዎች በአድማው እየተሳተፉ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎TaxiDriversStrike‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኦሮሚያ የአውቶብስ መናኽሪያዎች ባዶ ሆነዋል::በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተስፋፍቶ በዛሬው እለት በወሊሶ …

የአዲስ አበባ ታክሲዎች አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ አሽከርካሪዎች በአድማው እየተሳተፉ ነው:: Read more »

የታክሲ ማህበር የጠራው የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት ለ2ኛ ቀን ቀጥሎዋል ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbeba‬ ‪#‎TaxiDriversStrike‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ መንግስት ያወጣውን የትራፊክን ህግ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን በመቃወም የታክሲ ማህበር የጠራው የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት ለ2ኛ ቀን ቀጥሎዋል የዛሬውም ተቃውሞ በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች …

የታክሲ ማህበር የጠራው የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት ለ2ኛ ቀን ቀጥሎዋል Read more »

የወልቃይት ፖለቲካና ተቃዉሞ በዳባት አካባቢ – ግርማ ካሳ የኢሕአዴግ መንግስት ላይ እየቀረበ ያለው ተቃዉሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በስሜን ጎንደር ዳባት ከተማና አካባቢ ተቃዉሞ እንደተነሳም እየሰማን ነው። ተቃዉሞው ወደ ወረዳዉና የቀበሌ መንደሮች እየተዛመተ እንደሆነ ነው ዘገባዎች የሚጠቁሙት። ዳባት ከጎንደር …

የወልቃይት ፖለቲካና ተቃዉሞ በዳባት አካባቢ – ግርማ ካሳ Read more »

የኦሮሞ ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት መንግስት የኦሮሞን ህዝብ እንዲያረጋጉ ተልከው በየሚዲያው እየወጡ ሲያስተባብሉ የከረሙት የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኦቦ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ኦሮሚያ የትምህርት ቢሮ ተዘዋውረዋል:: በርሳቸው ቦታ ላይም በሕወሓት መንግስት ተላላኪነታቸው “ኦቦ ገብረመድህን” የሚል ስም የተሰጠው አቶ በከር ሻሌ ይህን ቁልፍ ስልጣን መረከቡን  ምንጮች ገልጸዋል:: አቶ በከር ሻሌ ከዚህ ቀደም […]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “ተሐድሶ” (ሪፎርሜሽን) ለማካሔድና በእነርሱ እምነት “ተባላሽቷል” የሚሉትን በመቀየር ገሚስ ፕሮቴስታንት ገሚስ ኦርቶዶክስ መሰል እምነት የመፍጠር ዓላማ መኖሩ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነታ ሆኖ “አለ ወይስ የለም?” በሚል ለምን ግር ይለናል? በሃይማኖታቸው ኦርቶዶክሳዊነት የማይጠረጠሩ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ልባቸው ይከፈላል። ለማመንም ለመተውም ይቸግራቸዋል። በሌላ አቀራረብ የሚቃወሙትን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትምህርት ለማስፋፋት የሚጥሩትን ተሐድሶዎቹን ሲረዷቸው ይገኛሉ። ይህ የመደናገርና ግርታ ላይ የመውደቅ አባዜ እጅግ ሥር ከመስደዱ የተነሣ በአገር ቤት ያለችውን ቤተ ክህነት እጅግ እግሯን አስሮ ሊቆጣጠራት ምንም አልቀረውም። ከአገር ቤቱ ተገንጥለን የራሳችን ሲኖዶስ አለን የሚሉትንም አባቶች እንዲሁ መጠቀሚያው አድርጓቸዋል። የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና የሆነው ይህ “ሪፎርሜሽን/Reformation” የተባለ አፈንጋጭ አስተምህሮ ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ለማይታያቸው ምናልባት የዚሁ ችግር ሰለባ የሆነችውን የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በአጭሩ መጥቀስ አብነት ሊሆን ይችል ይሆን?

የሕንድ ኦርቶዶክሶች ከቅ/ቶማስ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚመዘዝ ረዥም ሃይማኖታዊ ታሪክ አላቸው። ልክ እንደኛዋ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በ17ኛው መ/ክፍለ ዘመን ወደ አገራቸው የገቡት ፖርቹጋሎች ባመጡት “ኦርቶዶክሳውያንን ካቶሊክ የማድረግ ዘመቻ” ብዙ መከራ ተቀብለዋል። ግማሽ ሕዝባቸውንም አጥተዋል። በእነርሱ እግር የተተኩት አዲሶቹ የሕንድ ገዢዎች እንግሊዛውያን በበኩላቸው ኦርቶዶክሶችን “አንግሊካን” ለማድረግ በነበራቸው ፍላጎት በገንዘባቸው “የቲዮሎጂ ኮሌጅ በማቋቋምና ራሳቸው ረዳት መስለው በመግባት” ኦርቶዶክስ መምህራንን ሊያፈራ የተቋቋመን መንፈሳዊ ኮሌጅ ለራሳቸው ዓላማ በመቀልበስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውባቸዋል። በዚህም ሰበብ “ማላባር ኢንዲፔንደንት ቸርች፤ ማላንካራ ማር ቶማ ሴሪያን ቸርች እና ሴይንት ቶማስ ኢቫንጄሊካል ቸርች” የተባሉ ሦስት የፕሮቴስታንት እምነት ክፍሎች ሊፈጠሩ ችለዋል።

ከሕንድ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው “ተሐድሶው” የተጀመረው በአንግሊካን እንግሊዞች እርዳታ፣ ቄስ ያውም የቲዎሎጂ መምህር በነበረ ሰው አማካኝነት ነው። ይህ “አብርሃም ማፕላን” የተባለ ግለሰብ ዘመዱ የሆነን ዲያቆን መንበረ ፕትርክናው ወደሚገኘው ወደ ሶሪያ የሐሰት ደብዳቤ አስይዞ በመላክ እና ጵጵስና እንዲቀበል በማድረግ ሐሳቡን ከግብ ለማድረስ ችሏል። ጵጵስናውን ተሳስተው የሰጡት ፓትርያርክ ነገሩ ስሕተት መሆኑን ዘግይተው ቢገነዘቡም የደረሰውን ጥፋት እና ስብራት ለመጠገን ሳይቻላቸው ቀርቷል። ችግሩን ለመፍታት ሕንድ ድረስ ቢጓዙም “የፈሰሰ አይታፈስ” ሆኖባቸው አልፏል።

ዛሬ ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያናችን በሁሉም ዘርፍ ተንሰራፍተው ተቀምጠዋል። በአገር ቤትም በውጪውም ሲኖዶሶች አይነኬ ከመሆን ደረጃ ደርሰዋል። የሚያራምዱት እምነት ተሐድሶ መሆኑ በሰፊው እየተነገረ ዲቁናም ቅስናም የሚሰጣቸው ጳጳስ አላጡም። ምንኩስናን እየተቃወሙ ለጊዜው የመነኩሴ ቆብ የደፉትም ጵጵስና ለመቀበል በአገር ውስጡም በውጪውም ተራ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ሰዎች እንደሚፈራው እስከ ጵጵስናው ማዕረግ ለመድረስ ከቻሉ በሕንድ የደረሰው በእኛም ላይ እንደማይደርስ ምንም ማስተማመኛ ማግኘት አይቻልም። የሕንዱ ተሐድሶ (“የማር ቶማ ቸርች”) በእምነት ከአንግሊካኖች ጋር አንድ መሆኑን አውጆ የራሱን ጎጆ እንደቀለሰው ሁሉ የኛዎቹም የራሳቸውን ጎጆ የማይቀልሱበት ምንም ምክንያት የለም። በሕንዶች ከ1880ዎቹ ጀምሮ የተከሰተውን ታሪክ ከ150 ዓመት በኋላ የተፈጠርን ሰዎች ተመልክተን ችግሩን መገንዘብ ለምን ያቅተናል?

የሶሪያው ፓትርያርክ ለተሐድሶዎቹ የመጀመሪያ ጳጳስ ማዕረጉን ተሳስተው እንደሰጡት ሁሉ ዛሬም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ መናፍቃኑን ማዕረግ በማዕረግ አድርገው በመንጋው ላይ በእረኛ ፈንታ ተኩላ የሚልኩባቸው ሰዎች ከፍ ያለ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባቸው ነበር።

በዚህ ወቅት የተሐድሶዎች ክፍል በቤተ ክህነቱ የተፈጠረው የአባቶች መከፋፈል ሰርግና ምላሽ ሆኖት ከዚህ ሲሉት ከዚያ፣ ከዚያ ሲሉት ከዚህ እያጣቀሰ ስሩን እያስፋፋ ሲሆን የአባቶች መከፋፈል እውነት የመሰለው ኦርቶዶክሱ ክፍል በዚህም በዚያም ወገን እየተጎዳ ከሁለት ያጣች ጎመን ሆኖ ተዘልሎ ተቀምጧል። የተሐድሶው ክፍል አገር ቤት ሲገባ ኢሕዴግን፤ ውጪ ሲወጣ ተቃዋሚውን እየመሰለ ዋና ዓላማው የሆነውን የኑፋቄ ስራ በሰፊው ያስፋፋል። “ፓትርያርካችን አቡነ መርቆርዮስ ናቸው” ሲል ይቆይና አቡነ ማትያስ የደገፉት ሲመስለው ተቀልብሶ ሲያመሰግናቸው ያመሻል። “አቡነ ማትያስ ፓትርያርኬ” ሲል የቆየው አገር ቤት ያለው ክንፋቸው ሲመቸው ደግሞ ውጪ ያሉት አባቶች ጋር ራት ሲበላ ይገኛል። በዚህም በዚያም ግን ቤተ ክርስቲያን እየደማች ነው። ይህ አዚም የሚለቀን መቼ ነው? የምንደናገረውስ እስመቼ ነው?

በዚህ ረገድ ፓትርያርክ አባ ማትያስ ቀደምቶቻቸው አድርገውት በማያውቁት መጠን እና ስፋት ቤተ ክርስቲያኒቱን ጅብ እያስበሏት ነው። አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት የተሐድሶዎችና የዚሁ ዓላማ መጋቢ የሆኑ ግብረ በላ ወዳጆቻቸው መጠቀሚያ ሆነዋል። በቤተ ክህነቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያስብል ደረጃ ከቅ/ሲኖዶስ ተነጥለው፣ ሲኖዶሳዊቱን ቤተ ክርስቲያን ኢ-ሶኖዶሳዊ አስተዳደር ተክለውባታል። ብዙ ሚሊዮን ሕዝቧ በረሃብና በችጋር የዓለም መሳቂያ መሳለቂያ በሆነበት ዘመን፤ የኑሮ ምሬት ያንገሸገሸው ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ግዛቶች ምሬቱን በሚያሰማበትና በዚሁ ሰበብ የሚያልቀው ምእመን የቀብሩን ስፍራ ባጣበበት በዚህ ወቅት “አስረሽ ምቺው” የቅንጦትና የዘረፋ ሰደድ ቤተ ክህነቱን አቀጣጥሎታል። ይህ ሁሉ ሰርግና ምላሽ የሆነው ግን ለተሐድሶው ኑፋቄ ነው። ይህ ሁሉ ነገር እንዴት ያደናግረናል? ለምንስ አንነቃም?

                                               

ቸር ወሬ ያሰማን፤

አሜን። 

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

News Ethiopia Wetatoch Dimts February 29,2016 መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=dPgDhKqrKKk]  

አዲስ አበባ የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ ፤ ከዚህ በኋላ ? ግርማ ካሳ ገዢዎች በሃረርጌ፣ በወለጋ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ በምእራብ ሽዋና ምእራብ አርሲ የተነሳዉን ተቃዉሞ ከፍተኛ ቁጠር ያለው የወታደር ኃይል በማሰማራት በመቶዎች የሚቆጠሩትን በመግደልና በሺሆች የሚቆጠሩትን በማሰር ተቃዉሞዉን በኃይል ለማፈን እየሞከሩ ነው። …

አዲስ አበባ የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ ፤ ከዚህ በኋላ ? ግርማ ካሳ Read more »

በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ በታክሲ ሹፌሮች አድማ ታጅቦ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎TaxiDriversStrike‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) እምቢ ለመብቴ ግፍ ይብቃ የሚለው ሕዝብ እየበረከተ ተቃውሞው እያሰማ መሆኑን እና መቀጠሉን ከኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክል የሚወጡ መረጃዎች የጠቆሙ ሲሆን ተማሪዎች …

በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ በታክሲ ሹፌሮች አድማ ታጅቦ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል:: በወሊሶ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ እየጋየ ነው። Read more »

[ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን አስጠሩት] –    ምን አዲስ ነገር አለ? –    ሪፖርቱ ነዋ፡፡ –    የትኛው ሪፖርት? –    ሰሞኑን የወጣው፡፡ –    በምን ላይ? –    በሕገወጥ ዝውውር፡፡ –    የሕገወጥ ዶላሩን ነው? –    እ… –    ለእነዚህ ኒዮሊብራሎች ግን የት እንሂድላቸው? –    ምን እያሉ ነው? …

ክቡር ሚኒስትሩ ከሹፌራቸው ሲነታረኩ ከትራፊክ ፖሊሱ ሲሞዳሞዱ ዋሉ:: Read more »

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር ተከሰቷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbeba‬ ‪#‎TaxiDriversStrike‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ ሹፌሮች የወያኔ አገዛዝ ያወጣውን የትራንስፖርት እና መንጃ ፍቃድ ሕግ በመቃወም የጠሩት የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት የአዲስ …

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር ተከሰቷል:: Read more »

  በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዶክተር ማይገነት ሽፈራሁ ሞት ምክንያት ከባድ ሐዘን ላይ ናቸው። ዶክተር ማይገነት ሽፈራሁ የዶክተር ጌታቸው መታፈሪያ ባለቤትና የትዕግስት፣የህሊናና የካሌብ እናት ነበሩ። ዶክተር ማይገነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብኣዊ መብቶች እንዲሰፍኑና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ያላሰሰ ጥረት ሲያደርጉ …

ታላቋ ምሁር ዶክተር ማይገነት ሽፈራሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ Read more »

በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ተቃውሞ ተሰምቷል::ተቃውሞውን አትኩሮት ለማሳጣት እና ለማጣጣል የሚደረጉ ሙከራዎች አልተሳኩም:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Harerge‬ ‪#‎MinilikSalsawiam‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች በወያኔው አገዛዝ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በመቀጠል በዛሬው እለት በሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች እንዲሁም በበደኦ …

በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ተቃውሞ ተሰምቷል::ተቃውሞውን አትኩሮት ለማሳጣት እና ለማጣጣል የሚደረጉ ሙከራዎች አልተሳኩም:: Read more »

የእግሊዝኛው ጽሁፍ አዘጋጅ ፡ዓለም ማሞ የአማርኛው ተርጓሚ፡ ቢላል አበጋዝ  “ፔንታጎን ያሰለጠናቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት፤ ክፉውን አጋዚ የተሰኘውን ልዩ ኅይልም ይጨምራል።” ኢንተር- ሴፕት ኤንድ ናሽናል ሴኩሪቲ ለተባለው ጋዜጣ መስራችና ቃል አቀባይ ከአሜሪካ መንግስት ክፍተኛ ምክር ቤት የፍርድ ኮሚቴ ዘንድ ቀርቦ ከሰጠው የምስክርነት …

የህወሃት ልዩ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት የአጋዚ አመሰራረት እና የእናት እንባ – (ጄረሚ ስከሂል) Read more »