በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች አለመረጋጋት እየታየ ነው
ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ አባላት በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ በከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘወትር አርብ የሚደረገውን የጁመአ ስግደት አስታኮ የተቃውሞ ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱ ይታወቃል። የፖሊስን መግለጫ ተከትሎ የድምጻችን ይሰማ …