ውሸት ክነነፍሱ

ውሽትከነነፍሱ ሳይሞት ሳይቀበር
ህያው እንደሆነ ተይዞ በከብር,፣
ዱላ ሳያርፍበት እርግጫ ወይ ጡጫ
ሰደብ ሳይደርስበት ጥፊና ግልምጫ፣
እጆቹ የኍሊት ታስረው በሰንሰለት
ባየው ደስ ይለኛል በነጻ ፍርድቤት፣
አሰብን ገንጥሎ ማን ሰጠ አሳልፎ
ለመንግስታት ማህበር በራሱ እጅ ጽፎ፣
በዘር ፖለቲካ ማን ህዝብን ለከፈ
ምላሱን ጎልጉሎ ማንስ ለፈለፈ፣
ማነው ተጠያቂው በካራ ለሞተው
ከገደል አፋፍ ላይ ለተወረወረው፣
በሰላማዊ ሰለፍ ለሞቱት በሙሉ
በአዲስ አበባና በየዘር ክልሉ፣
ማነው ተጠያቂው ሰው ነው ወይስ ውሸት
ዕውነት የሌለውን ያገኘው አንደበት፣
ዕውነት እንዲነግስ ውሸት እንዲኮስስ
በነጻ ፍርድ ቤት ውሸት ሳይከሰስ
ሞቱን አያሳየኝ ዘላለም እንዲአለቅስ፣