በወላይታ የአንድነት ሰብሳቢ ታሰሩ – ፍኖተ ነጻነት
በወላይታ የአንድነት ሰብሳቢ ታሰሩ
በደቡብ ክልላዊ መስተዳደር ወላይታ ዞን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሰብሳቢ ታሰሩ፡፡ ሰብሳቢው አቶ ወኖ መንዓሳ ትናንት ነሐሴ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የዞኑ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑትንና ባለፈው ሳምንት ሐምሌ27 የታሰሩትን ወ/ሮ ሀዲያ መሐመድን ለመጠየቅ ከሚኖሩበት በዴሳ ወረዳ ወላይታ ሶዶ ከተማ ደርሰው ሊመለሱ ሲሉ ከአውቶቡስ ተራ ተይዘው መታሰራቸውን የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በፊት አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. በወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት ተይዘው የታሰሩት ወ/ሮ ሀዲያ መሐመድ በወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን ከስብሰባው በኋላ ደግሞ በዞኑ የፓርቲው ሰብሳቢ አቶ ወኖም እዛው መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በሁኔታውም አንድ ሻለቃ ጉዳዩን በቅርበት እያዩ ስለነበር መታሰራቸው አግባብ እንዳልሆነ የምስክርነት ቃላቸውን ቢሰጡም ታሳሪው ግን እንዳልተፈቱ መረጋገጥ ተችሏል፡፡ #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ #Wolayitasodo