የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ፌስቲቫል በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመሪያው አመታዊ ፌስቲቫሌ አርብ ጁሊይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ።

አያሌ ኢትዮጵያዊያን በጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ፡ አርት ጋለሪ የተገኙት ከዝግጅቱ ከመጀመሩ ቀደም ብለው ሲሆን፡ ለሶስት ቀናት የሚካሄደው ይህ ፌስቲቫል የተከፈተው፡ መክብብና አምሳሌ የተሰኙ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሰዓሉያን ባቀረቧቸው አስደናቂና ማራኪ የስእል ስራዎች፡ እንዱሁም በአርበኞች ፎቶግራፎች ነው።

በመቀጠልም፡ በጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ የአርት ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ክሉፎርድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። እንዱሁም የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ሊቀመንበር አቶ ሼክስፒር ፈይሳም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አሰምተው፡ ረጅም ግዜ ከኢትዮጵያዊያን አይን ተሰውራ የቆየችውና የዚህ ፌስቲቫሌ የክብር እንግዳ የቀድሞዋ የፖለቲካ እስረኛ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በመክፈቻው ዝግጅት ወደ አዲራሹ መግባቷ፡ በተነገረ ግዜ ከፍተኛና የማያቋርጥ ጭብጨባ ተሰምቷል።

የመጻህፍት ፍርሚያ፡ የግጥም ንባቦች፡ የታሪክ ማስታወሻዎችና የሙዚቃ ቅምሻዎች በታዋቂ ገጣምያን የቀረቡ ሲሆን፡ አርቲስት ማርታ ቀጸላ፣ አርቲስት መኮንን፣ ኢትዮጵያዊው የአለምአቀፍ ኦልምፒክ ኮሚቴ የቀድሞ ባለስልጣንና ‘የፒያሳ ልጅ’ የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ፡ አቶ ፍቅሩ ኪዲኔም አጭር ንግግር አድርገዋል። ዝግጅቱን ለመከታተል የመጣው ሰው ከአዲራሹ ጋር  ባለመመጣጠኑ የተነሳ፡ ብዙ ሰዎች ከውጭ እንዲቆሙ የተገደደ ሲሆን፡ ይሄንን የተመለከተውና በዚህ ዝግጅት የተደሰተው የጥበብ ባለሙያና ጋዜጠኛ አበበ በለው፡ “ይኼ ዝግጅት በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥል፡ እንደውም አንድ ዋና መንገድ አስዘግተን የኢትዮጵያ ቀን መከበር አለበት” ብሏል።

በዚህ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ ብዙ ኢትዮጵያዊነትን ያስታወሱ ስሜት ቀስቃሽ ስራዎች ቀርበዋል።

የፌስቲቫሌ ዝግጅቱ ቅዲሜ ጁሊይ 2 የሚቀጥል ሲሆን፡ ከጠዋቱ ከ9 ሰዓት የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከአትላንታ፣ ከቨርጂኒያ ከባልቲሞርና ከዲሲ በተውጣጡ ቡድኖች ይካሄዳል።

ከሰዓት በኋላ የቡና ስነስርአት፣ የላጆች አምባ ዝግጅት፣ እንዱሁም በዋንኛነት የቅኝት የባህል ሙዚቃ ቡድን ባህላዊ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል። የመካከለኛና አጭር ርቀት የሩጫ ውድድርም ይካሄዲል። ይኸው የእግር ኳስ ጨዋታውና የሩጫ ውድድሩ እሁድ እለትም ቀጥሎ ይውላል።

እሁድ ጁሊይ 3 ቀን ታዋቂዎቹ ድምጻዊያን ብርሃኑ ተዘራ፡ አበባ ደሳለኝ፡ እና መስፍን ዘበርጋ በሚገኙበት የሙዚቃ ኮንሰርት ይዘጋል።

በሁለቱ ቀናት ዝግጅት ነጻ የመኪና ማቆሚያና፡ ለእግረኞችም ከፎጊ ቦተም ወደ ስቴዱየሙ የሚያመላልስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተሰናዳ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል። የዝግጅቱን ሂደት እየተከታተልን እንዘግባለን።

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ድርጅት በሰሜን አሜሪካ፡ የኢትዮጵያዊነትን ውርስ ለማስጠበቅና ኢትዮጵያዊነትን ለመጠበቅ የተቋቋመ መንግስታዊ ያሌሆንና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።

አርብ ጁሊይ 1፡ 2011 ዓ.ም. ዋሽንግተን ዱሲ፡ ተክሇሚካኤሌ አበበ