ኢትዮ ቴሌኮምና ሠራተኛ ማኅበሩ በሕጋዊ ጥያቄዎች ላይ ተፋጠዋል
‹‹የሠራተኛውን መብት በሕግ ለማስከበር ዝግጅታችንን ጨርሰናል›› የሠራተኛ ማኅበሩ
‹‹የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች መሠረታዊ ማኅበር የሚባል የለም›› ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞውን ማኔጅመንት ሙሉ በሙሉ ከተረከበበት ከታኅሣሥ 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ያደረጋቸው የሠራተኛ ቅነሳና የሥራ ሁኔታ ለውጦች፣ በአገሪቱ የተደነገጉ ሕግጋትን ያልተከተለና ኢትዮጵያም የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚጥስ መሆኑን፣ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበሩ ሰኔ 23 ቀን 2003 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡