ዜና ከወላይታ፤ አንድነት ፓርቲ በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን ሞቅ ባለ ሁኔታ ጀምሯል – ፍኖተ ነጻነት
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ያዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ እንይካሄድ ከፍተኛ ወከባ ፣ ጫና እና ውንብድና ቢደረግም የዞኑ አመራሮች የደረሰባቸውን ተደጋጋሚ እስርና አፈና በመቋቋም በአሁኑ ሠአት ጫናውን ጥሶ ከመጣው ሕዝብ ጋር ስብሰባው እየተደረገ ይገኛል፡፡
አንድነት ፓርቲ በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን ሞቅ ባለ ሁኔታ ጀምሯል። ስብሰባውን የከፈቱት የአንድነት አመራር ይህን ሁሉ አፈና እና ማስፈራራት ተቋቁሞ በአዳራሹ የተገኘውን ህዝብ “ጀግኖች ናችሁ” ሲሉ አወድሰዋል። ወ/ሮ ሀድያ የሚባሉ የአንድነት አመራር አባል በቅስቀሳ ወቅት ተይዘው እንደታሰሩና አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ስብሰባውን የሚመሩት የአንድነት አመራሮች ለህዝቡ ይፋ አድርገዋል። #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ