ሰበር ዜና፤ ከአርባምንጭ እና ጂንካ – ፍኖተ ነጻነት

ሰበር ዜና፤ ከአርባምንጭ

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ከከተማው የመንግስት ኃላፊዎች ጋር የተሳካ ውይይት ተደረገ!!

አቶ አበበ አርባ የአርባምንጭ ከንቲባ፣ ኮረኔል ዳንኤል አረጋ የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ እና ዳንኤል አጀቤ የፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ከ አንድነት የሰልፉ አስተባባሪዎች ከአቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ ፣ ሻለቃ አርጋው እና አቶ ክፍሌ ትንቧለል የጋሞ ጎፋ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ እልህ አስጨራሽ ውይይት በኃላ ስምምነት ላያ መድረሳቸውን አሳወቁ፡፡

የአርባምንጭ ከተማ የመንግስት ኃላፊዎች የጸጥታዉን ሁኔታ አስተማማኝ እንደሚሆን መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ በአንድነት ፓርቲ በኩልም ሰልፉ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡

ሰበር ዜና፤ ጂንካ

በጂንካ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ከከተማው የመንግስት ኃላፊዎች ጋር ስለነገው ሰላማዊ ሰልፍ ውይይት እያካሔዱ ነው ቅስቀሳው በመኪናና በሞተር ቅስቀሳ በሰፊው ቀጥሏል፡፡

‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬
544512_493761017375504_998393223_n