ሰበር ዜና፤ – በአዲስ አበባ በርካታ ሙስሊሞች በፌደራል ፖሊሶች እየታፈሱ ነው
በጦር ኃይሎች፣ ቤትል ጎጃም በረንዳና መሳለሚያ ከመስጊድ የወጡ ሙስሊሞች ታፍሰዋል፡፡ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በርከት ያሉ ፌደራል ፖሊሶች ይታያሉ፤ ከሌሊቱ 5 ፡00 ሰዓት ጀምሮ መኪናዎች ላይ ከባድ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው፡፡ የሙስሊሙን የመብት እንቅስቃሴ የሚመራው ድምፃችን ይሰማ የተባለው የሶሻል ሚዲያ ግሩፕ ከቤተመንግስት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ብሶቱን እንዲያሰማ ጥሪ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡