ሰበር ዜና የአረና ትግራይ ና የአንድነት አባላት መቀሌ ውስጥ ታሰሩ

መድረክ ነገ ሐምሌ 14 በመቀሌ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ በመኪና ሲቀሰቅሱ የነበሩት የአረና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ህሺ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀኔ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የአረና ፓርቲ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ጨምሮ እንዳስታወቀው ለነገው ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳይደረግ የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች ክልከላ ቢያደርጉም በነገው እለት ስብሰባው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ማጋጃ ቤት አዳራሽ ውስጥ ይደረጋል፡፡