የመሬት ሽያጭ ለልማት ወይንስ ለአገር ጉዳት?
ግርማ ካሣ ([email protected])
የሕንድ፣ የቻይናና የሳውዲ ኩባንያዎች በአገራችን ኢትዮጵያ ለእርሻ ሥራዎች ሰፊ መሬት በሊዝ እንደወሰዱ በስፋት ተዘግቧል። የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት «ሰዎች የማይኖሩባቸው ቦታዎችን ነው ለልማት ስንል ለውጭ አገር ዜጎች የሰጠነው» ይላሉ። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ያለ ውዴታቸው ዜጎች እንደተፈናቀሉ፣ ከመኖሪያቸው እንደማይፈናቃሉ የሚናገሩት እንደሚታሰሩና እንደሚገደሉ፣ የመሬቱም “ሽያጭ” በርካሽ ዋጋ፣ እስከ 99 አመታት ላለ ረጅም ጊዜ እንደሆነ በመግለጽ፣ የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግን እንቅስቃሴ ጸረ-ሕዝብና የአገርን ጥቅም የሸጠ እንደሆነ አድርገው ያቀርባሉ።