እንደ ዔሳው ብኩርናቸሁን ለሸጣችሁ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (አሮን)

ኪነጥበብ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያላትን ሚና ራሳቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹ ቢነግሩን የተሻለ ይሆን ነበር

አሮን

ዛሬ ግን በአዲስ አበባ ከተማ የታዘብኩት የአርቲስቶች ትያትር አንድ ነገር እንድል ግድ ብሎኛል። ኪነጥበብ የአንድን ማህበረሰብ የነጻነት መንፈስና የሞራል እሴቶች ለመገንባት የምትጫወተውን ሚና ለአርቲስቶቹ ማስታወስ ተገቢ ሁኖ አግኝቼዋለሁ። አንድ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ወደዚህ ክቡር ሙያ ሲሰማራ ማህበረሰቡ በሚኖርበት ጉድፍ ውስጥ ሊኖርበት ሳይሆን ያንን ጉድፍ አጽድቶና አስተካክሎ ንጹህ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የላቀ ሚና ለመጫወት ነው። የኪነ ጥበብ ሰው ክብርና የህዝብ ፍቅር የሚኖረው በማህብረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ነውሮችንና ጉድፎችን ሲነቅፍና ለማረም ሲሞክር እንጂ በዚያ ነውር ውስጥ ራሱ ተዘፍቆ ሲኖርበት አይደለም።