ያራ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

– አንድ ቢሊዮን ዶላር በጀት ተይዟል

ላለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ ማዳበሪያ ሲያቀርብ የቆየው ያራ ሆልዲንግ፣ ከህንዱ ሴፍቴክ ኩባንያ ጋር በሽርክና ባቋቋመው ኢትዮ ፖታሽ ኩባንያ ስም በአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ለማምረት የፈቃድ ጥያቄ አቀረበ፡፡