የኪሎ ሥጋ ዋጋ ጣሪያ 90 ብር እንዲሆን ልኳንዳ ነጋዴዎች ወሰኑ

– ውሳኔው የሸማቾች ጥበቃና የንግድ አሠራር አዋጅን የጣሰ ነው

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች በትናንትናው ዕለት ጠቅላላ ስብሰባ አድርገው በግብይይት ሥርዓቱ ላይ በሰፊው ከተወያዩ በኋላ፣ የአንድ ኪሎ ሥጋ የዋጋ ጣሪያ ቫትን ጨምሮ 90 ብር እንዲሆን ተስማሙ፡፡