የቅድስት ሥላሴ መ/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በነገው ክብረ በዓል ችግራቸውን ለምእመኑ ያሰማሉ፤ የቋሚ ሲኖዶሱ አብዛኞቹ አባላት ያለምእመናን ንቅናቄ ችግሩ መፍትሔ እንደማያገኝ ያምናሉ
admin
Tagged with addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
- ደቀ መዛሙርቱ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን የኮሌጁን የምግብ ቤት አገልግሎት ተከልክለዋል
- የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ደቀ መዛሙርቱ ወደ ክረምት ዕረፍት ከመሄዳቸው በፊት የማጠቃለያ ፈተና እንዲወስዱና ተመራቂዎቹ እንዲሸኙ ጥረት እያደረገ ነው፤ በፓትርያሪኩ የመወሰን አቅም ላይ ጥርጣሬ የገባቸው የሚኒስቴሩ ሓላፊዎች ልዩ ጽ/ቤቱ ደቀ መዛሙርቱን በኀይል ከኮሌጁ ለማስወጣት ያቀረበውን የድጋፍ ጥያቄ ውድቅ ባደረጉበት አቋማቸው ጸንተዋል
- ፓትርያሪኩ በሚይዟቸው አቋሞች ረዳት ሊቀ ጳጳሱ አቡነ እስጢፋኖስ ከአቡነ ጢሞቴዎስ ጋራ የእንደራሴነት ሚና እየተጫወቱ መኾኑ እየተነገረ ነው
- አቡነ ጢሞቴዎስ በኮሌጁ ያላቸው ሥልጣን በግልጽ እንደማይታወቅ ለአጣሪ ኮሚቴው የተናገሩት የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ኮሌጁ ‹‹ጠንካራና ውሳኔ የሚሰጡ የአስተዳደር ሰዎች›› እንደሚያስፈልጉት ጠቁመዋል
- አጣሪ ኮሚቴው÷ የኮሌጁ አስተዳደር ራሱን ለማረም ዝግጁ እንዳልኾነ ተገንዝቧል፤ ኮሚቴው በየዘርፉ ለታዩ የአሠራር ክፍተቶች በሪፖርቱ ያቀረባቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ የማስተካከያ ርምጃዎች በአስቸኳይ ይፈጸሙ ዘንድ የሚመለከተው የበላይ አካል መመሪያ እንዲሰጥበት ጠይቋል
