Re: ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ? !



የትምህርት ጉዞው የተጠናቀቀ ይመስላል፡፡ ተማሪዎች በምረቃ ቀን የሚለብሱትጋወን አስመራቂ ቤተሰቦቻቸው ወደ ምረቃውቦታ የሚገቡበት የመግቢያ ትኬት ከየትምህርት ክፍላቸው እየወሰዱ ነው፡፡ አንድ ከዚህበፊት ያልተለመደ ተግባር ግን ይቀራል፡፡ የአንድ ሙሉ ቀንስልጠና፡፡ ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት በመጡ ባለሙያዎችከምረቃ በኋላ ሊሰማሩባቸው ስለሚችሉባቸው የስራ አይነቶች፡፡

ገነትም ከነዚህ ሰልጣኞች መካከል አንዷ ስትሆን 3 አመትየዩንቨርስቲ ቆይታዋ Applied Biology ያጠናች ስትሆን ከተቻለ አንድ ፋርማሲ ውስጥ ሰራተኛሆና ለመቀጠር አለዚያም መምህር እሆናለው የሚል ህልም ነበራት፡፡በስልጠናው የሰማችው የስራ መስክ ግንአልተዋጠላትም፡፡ ተደራጅቶ የባልትና ውጤቶችን መሸጥ፣ የከተማ ግብርና ላይ መሰማራት፣ የኮብል ስቶን ማንጠፍስራ፣ ፓርኪንግ ..ተ፡፡

አሁን ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት ተማሪዎችን ከሚያስተምሩት የዩንቨርስቲ መምህራን አንዱ የሆኑት አቶ ዳዊት ገብሩ (ስማቸው የተቀየረ) ግን የምሩቃኑ ብቃት አሳስቧቸዋል፡፡ አቶ ዳዊት የሚያስተምሩት የሞራል ፍልስፍና ትምህርት ሲሆን፤ ሰሞኑን የመጨረሻ ፈተና ለተመራቂ ተማሪዎቻቸው የፈተኑት ሲሆን አንድ የፈተና ወረቀት ግን ይጠፋባቸዋል፡፡ የመጥፋቱን ምክንያት ሲያጣሩም ኩረጃን ለመቀነስ በማሰብ ተማሪዎች ከሌላ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ጋር ተደባልቀው የሚፈተኑ በመሆናቸው እና ፈተናው የጠፋባት ተማሪ የማታውቀውን የሶሻል አንትሮፖሎጅ ፈተና ተፈትና በመውጣቷ መሆኑን ይደርሱበታል፡፡ አቶ ዳዊት ተማሪዋን አስቀርበው ለምን እንዳልተፈተነች ሲጠይቋት፤ እንግሊዝኛ ማንበብ እንደማትችል እና የተፈተነችው ፈተናም የሞራል ፊሎሶፊ ፈተና እንደሆነ አስባ እንደተፈተነች ትናገራለች፡፡

የዲግሪ ምሩቋ የምትፈተነውን ፈተና አለማወቋ አቶ ዳዊትን ግራ ከማጋባትም አልፎ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡ እናም ትምህርት ወዴት ወዴት? ብለን እንጠይቅ ዘንድ ተነሳን፡፡
 
ትምህርት

የሰው ልጅ ሁሉን ያውቅዘንድ አይቻለውም ስለዚህም ስለ ክዋክብቱ መረዳቱ የበዛለት ላላወቀው እሱም ስለስነ ተዋልዶ እውቀቱ ከሌለው ከአዋቂው የሚቀስምበት ስርዓት ነው ትምህርት፡፡ አንድ ሰውአቃቂ ምሁር ይባል ዘንድበሁሉም የትምህርት ዘርፎች የዕውቀት ላቂያ ይኑረው ያኔም አዋቂይባላል፤ ይለናል Renaissance Man ሕልዮት፡፡ ለዛም ይመስላልበአብርሆትዘመን  የነበሩ ምሁራን ሁሉን አቀፍእውቀት ነበራቸው ልንል የምንችለው፡፡ የፍልስፍና፣ የሂሳብ፣ የስነክዋክብት፣የስነሰብ .. እውቀቶችን አንድ ምሁርአቅፎ ሊይዝ ይችል ነበር፡፡

ይሄ ትክክል አይደለም ይልቅስ በህብረተሰቡ ውስጥ እምርታ ይመጣ ዘንድየስራ ክፍፍል (Division of Labor) ወሳኝ ነው ብሎስኮትላንዳዊው የስነምጣኔ ምሁርአዳም ስሚዝ የሀሳብ ሽግግር ካደረገ ወዲህ፡፡ እያንዳንዱ ህብረተሰቡ አካል አንድየስራ መስክ ላይ በተለየ (Specialize) አድርጎ ጥናት ካደረገ እና ከተማረበዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያመጣል በሚል የትምህርትስርዓቶቹም በዚህ ሀሳብ መቀረፅጀመሩ፡፡ ባጫ ምህንድስና አበበህግ አይዳ እርሻ.. እየተማሩበያዙት ሙያ ላቂያን ማሳት ይችላሉየሚለው Specialization ሕልዮት፤ አሁን ድረስ በትምህርቱዘርፍ ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡

ሱፍ ለባሽ ምሁር

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ መቶ አመትእንኳን አልደፈነም ፡፡ የመጀመሪያው ዘመናዊ የመንግስት ትምህርት ቤት 1908 ነው የተቋቋመው እስከ ጣልያን ወረራም ብዙ ተማሪዎችንማስተማር አልተቻለም በአብዛኛውም ከውጭ ተምረው የመጡ ኢትዮጵያዊያን ነበሩእንደ ምሁር የሚቆጠሩት፡፡ ከነዚህ በውጭ ተምረውየመጡ 120 ተማሪዎች ውስጥ ጣልያን በተለምዶ የሚያዚያ 28 ጭፍጨፋተብሎ በሚጠራው ድርጊት 75 በመቶዎቹን እንደ ገደላቸው የመንግስትን ሪፖርት ጠቅሰው Mrgery Perham, The Government of Ethiopia ባሉት መፅሃፋቸውያስረዳሉ፡፡

እንግዲህ በጣሊያን ወረራ 75 በመቶ የተማረሀይሏን ካጣች በኋላ እስከንጉሱ የስልጣን ዘመን ማክተሚያ ድረስ የተማሪዎችቁጥር (በውጭም በሀገር ውስጥም ተምረው የመጡት) በብዙ እጥፍ ጨምሯል፡፡ ነገር ግን አውሮፓን አይቶ የመጣው ምሁር ብዙ ፈተናዎች አጋጥመውታል፡፡ ከዋና ፈተናዎች አንዱ በተማረበት መስክ ስራ ያለማግኝቱ ነው፡፡ አለ ከተባለ የፈረንሳይ ህግ ትምህርት ቤት ህግ ተምሮ የሀረርጌ አውራጃ አስተዳዳሪ የእልፍኝ አሽከር፣ Literature 4 ዓመት ሙሉ እነ ሸክስፒርን እነ ሞንታኝን፣ እነ ዳንቴን እንዲያም ሲል እነ ቶልስቶይን ሲያጠና ከርሞ በንግድ ሚኒስቴር የወርሃዊ የዋጋ ጥናት ባለሙያ መሆን፣ የምጣኔ ሀብት ትምህርትን እንደ ውሃ ጨልጦ በበጌምድር አውራጃ የደምቢያ ወረዳ የመንግስት ሹም .. እየሆኑ ነበር እነዚህ እውቀትን እና አለባበስን ከአውሮፓ የቀዱ ምሁራን ወደ ስራ አለም የሚሰማሩት ፡፡


በርግጥ   ትውልድም  የዚህ ሱፍ ለባሽ ምሁር አካል ነበር፡፡

የተማረ ሁሉ ያስተምር

ደርጉ መጣ‹ሁሉንም ነገር ወደ ጦርግንባር; ከማለቱ በፊት የትምህርት ዘመቻ ጀመረ‹መሃይምነት አይነስውርነት ነው› በሚል መፈክርየገጠሩን ህዝብ ስሙን ይፅፍዘንድ ፊርማ በእርሳስ ይፈርም ዘንድ አስቻለው፡፡ነገር ግን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ ተማሪወች የተማሩትን ትምህርት የት አደረሱትከተባለ፤ ግማሾቹ አቢዮት ጠባቂ፣ ግማሾቹ የቀበሌ ሹም ወታደርቤትም የገቡ አሉ፡፡

ይልቁንም ደርጉ ተማሪዎችን ከነ ኢህአፓ ጋርንክኪአላቸው በሚል በጥርጣሬ ነበር የሚመለከታቸው፡፡ ይባስብሎም ከሀገር በፊት የምን ትምህርትብሎ በተለምዶምሁሩ ጦርየሚባለውን ወታደር ከዩንቨርስቲ አፍሶ ብላቴ ጦርማሰልጠኛ ከተተ፡፡ የተማሩት ትምህርትም አላማው ጠፋባቸው ለነዚህ ምሁር ወታደሮች፡፡

ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ?!

ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ከሰራቸውአመርቂ ስራዎች አንዱ ትምህርትን በነፃ ተደራሽለማድረግ ያደረገው ጥረት እና ያምያመጣው ውጤት ነው፡፡ አጠቃለይ የትምህርት ፖሊሲ 1986 . ከወጣ በኋላ ብዙአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተሰርተዋል፣ የትምህርት ቤቶች የቅበላአቅም በብዙ እጥፍ ጨምሯል፣30 በላይ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ተገንብተዋል፡፡

ነገር ግን የትምህርት ፖሊሲውን ሁለት ዋነኛተግዳሮቶች አንቀው ይዘውታል፡፡

1. የትምህርት ጥራት ጉዳይ፡

መንግስትም እንደሚለው ዋነኛው የትምህርት ፖሊሲያችን ፈተና የጥራት መጓደል ነው፡፡ አሁን ባለውሁኔታዩንቨርስቲ Chemistry ምሩቅ ተማሪዎች Chemistry Khemistry እያሉ እንደሚፅፉ ይነገራል፤ አራቱን የሂሳብ ስሌቶች የመለየት ችግርም የምሩቃኑ ሌላው ጣጣ ነው፤ በሶሲዎሎጅ ተመርቀው ካርል ማርክስ ሲባል እሱ ደግሞ ማነው? ማለትም ያስደነግጣል፤ ህግ ተምረው Civil Right እና Civil Code ነትን አለማወቅም ይወራል፡፡
አዎ ጥራቱ ችግር ውስጥነው፡፡

2. ሁለተኛው እና አዲሱ የትምህርትፖሊሲው ችግር ሰዎች ተምረውበተማሩበት ትምህርት መስክ ሊሰሩ አለመቻላቸውነው፡፡

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን 2011 .የከተማ ስራ አጥነት 18 በመቶ እንደሆነመረጃው ያስረዳል ፡፡ሌሎች አለማቀፍ ተቋማት ደግሞ መጠኑከዚህ እንደሚልቅ ይገልፃሉ፡፡


እንግዲህ ከዩንቨርስቲ የሚወጡት ምሩቃን ከነዚህ ስራ አጦች ቁጥርላይ የሚደመሩ ናቸው፡፡ ይሄን ቁጥር ለመቀነስይመስላል መንግስት ሰሞኑን እንደምንሰማው ወጣቶችን በተለያዩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ተግባራት ላይ እንዲሰማሩእያደረገ የሚገኝው፡፡ ችግሩ ግን አንድ ሰው Computer Science ተምሮ የኮብል ስቶን ጠረባ ላይ የመሰማራቱን ጥቅም ስናሰላስለው ነው፡፡ ችግሩ ግን አንድ ወጣት Physics ተመርቆ በከተማ ግብርና ተግባር ላይ ሲሰማራ የተማረውን ትምህርት ተግባር ላይ እንዴት ሊያውለው ይችላል? ያልን እንደሆነ ነው፡፡ ችግር የሚሆነው Afan Oromo & Literature የተማረች ወጣት በባልትና ውጤት ስራ ላይ ተሰማርታ ስናይ ነው፡፡

ለመሆኑ: ይሄ ስኬት ነው እንዴ?


Nelson Mandela
በግለታሪካቸው ላይ ስለ ትምህርትሲናገሩ :

“Education is the great engine of personal development. It is through education that the daughter of a peasant can become a doctor, that a son of a mineworker can become the head of the mine, that a child of farm workers can become the president of a nation.”

አሁን ወዳለው ሀገራችን የትምህርት ውጤት ስንሄድ ማንዴላ እንደሚሉት ትምህርት የገበሬውን ልጅ ዶክተር የማዕድን ቆፋሪውን ልጅ የሀገር መሪ የሚያደርግመሳሪያ ነው ያሉትን የትምህርት Upgrade የማድረግ ሚና Downgrade በማድረግየተተካ ያስመስለዋል፡፡ አለዚያማ ስለ ፓለቲካል ህልዮት ሲማር የከረመወጣት እንዴት የብየዳ ስራ ላይ ይሰማራል?፡፡

ገነትስለ ስራ አስበሽ ታወቂያለሽ?›› ተብላ ስትጠየቅ ‹‹እኔ የምማረው እናቴ ተመርቄ ስታየኝ ደስ እንዲላት ነው እንጅ ስራ መስራት አልፈልግም›› ትላለች፡፡ የሞራል ፍልስፍና ፈተናን ከሶሻል አንትሮፖሎጅ ጋር ጋር መለየት አቅቷት ፈተናውን ሳትወስድ ቀረችው ምሩቅ ለስህተቷ የምትሰጠው ምላሽ ፈገግታ ነው፡፡ እንግዲያውስ ገነቶችን ከምሁራን መካከል መፈለግ ምን ይሆን እርባናው?