የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ዓቅም ዋጋ ከ20 በመቶ በላይ መውረዱ ታወቀ። እርምጃው የዋጋ ግሽበቱን በማናር የኑሮ ውድነቱን እንደሚያባብስ ይሰጋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነሃሴ 25 ቀን 2002 ባወጣው መግለጫ 13 ብር ከ 62 የነበረው አንድ የአሜሪካ ዶላር ኦፍሴላዊ ሚንዛሪ ወደ 16 ብር ከ67 ሳንቲም ዝቅ ማለቱ አስታውቆአል።፡ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሥልጣን ላይ ከመምጣቱ 1983 በፊት የአንድ የአሜሪካን ዶላር ሚንዛሪ ዋጋ 2 ብር ብቻ የነበረ ሲሆን ባለፉት 19 አመታት የብር ዋጋ በተከታታይ ቁልቁል እየወረደ መጥቶ አሁን ከደረሰበት 16 ከ 67 መድረሱ እጅግ የሚያሳስብ ነው ተብሎአል። አንዳንድ የገቢያ ሙያተኞች የአሁኑ የዋጋ ግሽበት እንደ ነዳጅና ማዳበሪያ የመሳሰሉ ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትን ምርቶች ዋጋ እጅግ በማናር የህዝባችንን የሁሮ ደረጃ የባሰውኑ ገደል ውስጥ እንደሚጨምር እየተናገሩ ነው። በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ በተከታታይ ባለ ሁለት አሃዝ እድገት በማስመዝገብ ልማታዊ መንግሥትነቴን እያረጋገጥኩ ነውና አርፋችሁ ተገዙ እያለ የሚሰብከው ወያኔ እና ጀሌዎቹ ይህንን በአደባባይ አፍጦ የወጣውን የህዝቡን ኑሮ ደረጃ ወደ አስከፊነት የሚለውጠውን የምንዛሪ ማሽቆልቆል በተለመደው ቅጥፈት ለማስተባበል ልማታዊ እድገታችን ተከትሎ የመጣ በረከት ነው ብለው ሊሞግቱ እንደሚሞክሩ ይጠበቃል።

አዲሱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሊያስከትል የሚችለውን ሥጋት ለማወቅ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ተዘዋውሮ ያነጋገረው ዘጋቢያችን፤ ወያኔ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በገጠመው ቁጥር እየተነሳ የሚያወጣው የተመን አዋጅ በተለይ በከተሜው ነዋሪና በሸምቶ አዳሪው ህብረተሰባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የዕቃ ዋጋ ንረትን ስለሚያስከትል ኑሮን ከዲጡ ወደ ማጡ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለመኖር ሲል ነጻነቱንና ክብሩን ሰውቶ የነበረውን ህዝብ በማስቆጣት ለሥር ዓቱ መውደቂያ ጉድጓድ መማሻም ሊሆን ይችላል መባሉን ዘግቦአል።