የደርግ የደህንነት ሚኒስትር ተስፋዬ ወልደ ስላሴ ሞተ

(ሪፖርተር) — በደርግ ዘመን የደህንነት ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደ ስላሴ ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም. (እ.አ.አ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዪ፡፡

ኮሎኔል ተስፋዬ በደርግ ዘመን በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተከሰሱትና በቅርቡም በመንግስት ውሳኔ መሰረት የተፈረደባቸው የሞት ፍርድ ከተነሳላቸው 23 ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት ውስጥ አንዱ ነበሩ፡፡

ኮሎኔሉ በደርግ ዘመን ለረጅም ጊዜ የደህንነት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡