የአሜሪካ አዲስ ፖሊሲ በአፍሪካ ላይ …

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በነደፉት የአሜሪካና የአፍሪካ ግንኙነቶች የሚመሠረቱበት አዲስ አቅጣጫና አካሄድ ከፍ ያሉ የምጣኔ ኃብት ዕድሎችን፣ ዴሞክራሲንና አፍሪካ መር የሆኑ የፀጥታ መፍትሔዎችን መደገፍና ማበረታታት እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡

በሦስት የአፍሪካ ሃገሮች ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኬፕ ታውን ላይ ትናንት ንግግር አድርገዋል፡፡

የሚስተር ኦባማ የኬፕ ታውን ንግግር የአሜሪካና የአፍሪካ መጭ ግንኙነቶች መሠረቶች ናቸው የተባሉ ግቦችን ያሣየ ስፋት ያለው ሥዕል ነው ተብሏል፡፡

ይህ የዩኤስ-አፍሪካ ፖሊሲ ድጋፍን ወይም እርዳታን፣ ንግድና መዋዕለ-ነዋይን፣ ጤናና የፀጥታ ትብብር አካባቢዎችን የሚሸፍን እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በፕሬዚዳንቱ አባባል የንግግራቸው ማዕቀፍ የተዋቀረው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ …