አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር በሰሜን አሜሪካ ሕዝባዊ ስብሰባ
አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 30ኛው አመት የስፖርትና የበዓል ዝግጅት ወቅት July 5 2013 ከ 11:30 AM ጀምሮ -እስከ 2:00 PM በDoubleTree Hotel Silver Spring ሜሪላንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ አቶ ብርሃነ መዋ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች፤ በፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍ ዙሪያ ፤ እንዲሁም በአገራዊና ወቅታዊ አሳሳቢ ክስተቶች ላይ አሰተተያየቶችን ያቀርባሉ።
የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ ተመስገን ዘውዴ ስለ አንድነት ፓርቲ ወቅታዊ ፈታኝ ሁኔታ ዙሪያ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ።
በተጨማሪም አቶ ዳንኤል ተፈራ ና አቶ በላይ በፈቃዱ በስካይፕ ከአዲስ አበባ ና በመላ ኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ስለመጣው የተቃውሞ እንቅስቃሴ፣ አንድነት በቅርብ ጊዜያት በአዲስ አበባና ሌሎች የኢትዮጵያ ትላልቅ ከተሞች ሊያደርግ ስላቀዳቸው የተቃውሞ ሰልፎችና በውጭ ያሉትን ኢትዮጵያውያንና የድጋፍ ማህበራት አንቅስቃሴና አዲስ የትግል አቅጣጫ አስመልክቶ ማብራሪያ ይሰጣሉ፣
በመሆኑም የአንድነት አባላት፣ ደጋፊዎችና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
የስብሰባው ቦታ፡8727 Colesville Road, Silver Spring, MD 20910
DoubleTree Hotel Silver Spring
የስብሰባው አዳራሽ፡ Chesepeek Hall
የስብሰባው ቀን፡ ጁላዪ 5፣ 2013
ሰአት፡ – 11am- 2pm
አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር