የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እያደረጉ ባሉት ጉብኝታቸው በሶዌቶ ስፋት ያለው ታዳሚ በተገኘበት የስብሰባ አዳራሽ ንግግር አድርገዋል፤ ከተሰብሳቢው ጋርም ተወያይተዋል፡፡